Thursday, December 31, 2015


የጎንደር ዩኒቨርስቲ 9ኛው የቱሪዝም ሳምንት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው፡፡




ዛሬ በዋናው ካምፓስ የባህል ፌስቲቫል ተካሂዷል፡፡ የሰሜን ጎንደርና አካባቢው መስህቦችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይም ከሰሜን ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር የቀረበ ሲሆን በጎንደር ከተማ ሆቴሎች መካከል የምግብ ዝግጅት ውድድር ተካሂዷል፡፡ የዘንድሮው በዓል መታሰቢያነቱ ለልዑል ራስ መንገሻ ስዩም አደረገ፡፡

Sunday, December 20, 2015



ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት ያከናወነቻቸው
የዘላቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ፡፡
ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር በኢትዮጵያ ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት ላለፉት 6 ዓመታት በአክሱም፣ በላሊበላና በአዲስ አበባና አካባቢዋ ሲከናወኑ የነበሩ ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ 

Thursday, December 10, 2015


                            አሹራ-ሀረሪዎች የሚያደምቁት ኩነት
 
 

አሹራ በሀረሪ በድምቀት የሚከበር ዓመታዊ ኩነት ነው፡፡ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የሆነው ሙሐረም በገባ በ10ኛው ቀን ይከበራል፡፡ አሹራ በሀረሪዎች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በርካታ ባህላዊ ክንዋኔዎች የሚያጅቡት የተለየ በዓል ነው፡፡ የበዓል አከባበሩ የተለየ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች አንዱ በየቤቱ በአዋቾች የሚዘጋጀው ገንፎ በቅቤ አንዱ ነው፡፡


                     ገዜ ጎፋ ወረዳ
 

ገዜ ጎፋ ወረዳ በጋሞ ጎፋ ዞን ከሚገኙ 2 ከተማ አስተዳደሮችና 15 ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ የወረዳው ዋና ከተማ ቡልቂ ስትሆን የተመሰረተችውም በ1918 ዓ.ም. ነው፡፡ የቡልቂ ከተማ ከተማው ወደ ሳውላ እስከ ተዛወረበት ማለትም እስከ 1955 ዓ.ም.  የድሮው የጎፋ አውራጃ ከተማም ነበረች፡፡
የገዜ ጎፋ ወረዳ በስተሰሜን ደምባ ጎፋና መሎ ኮዛ ወረዳዎች፣ በስተምስራቅ ደምባ ጎፋና ኦይዳ ወረዳዎች፣ በስተደቡብ ደቡብ ኦሞ ዞንና ኦይዳ ወረዳ፣ በስተምዕራብ ባስኬቶ ልዩ ወረዳና መሎ ኮዛ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡ ወረዳው ከአዲስ አበባ በ531 ኪሎ ሜትር፣ ከሀዋሳ 319 ኪሎ ሜትር፣ ከአርባ ምንጭ 267 ኪሎ ሜትር፣ ከወላይታ 148 ኪሎ ሜትር ከሳውላ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የወረዳው አየር ንብረት በሶስት አግሮ ኢኮሎጂካል ዞኖች የሚከፈል ሲሆን ደጋ 21.5 በመቶ፣ ወይና ደጋ 70 በመቶ፣ ቆላ 8.5 በመቶ ነው፡፡ አማካይ የሙቀት መጠኑ ደግሞ 23 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሲሆን የዓመቱ አማካይ የዝናብ መጠን 1300 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡

Tuesday, November 17, 2015


ድሬደዋ በሀገር ደረጃ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን እያስተናገደች ነው፡፡





እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንሳና ባህል ድርጅት በወሰነው መሰረት በየዓመቱ ኖቨምበር 16 ቀን የዓለም የመቻቻል ቀን ሆኖ በአባላ ሀገራቱ ይከበራል፡፡ አባል ሀገራቱም በዓሉን በተለያየ መልኩ ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡ ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህንን በዓል ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ከህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆይ ዝግጅት እያከበረችው ነው፡፡

Saturday, November 7, 2015

የሆቴሎች ኮከብ ደረጃ ምደባ ይፋ ሆነ



የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባሩት መንግስታት የዓለም ቱሪስት ድርጅት ጋር በመሆን ከሚያዚያ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርቶችን በኮኮብ ደረጃ የመመደብ ስራ የጀመረና በቅድሚያም የአዲስ አበባ ከተማ ሆቴሎች ጊዜያዊ የደረጃ ምደባ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

   ከጊዜያዊ የደረጃ ምደባው በኋላ በምደባው ቅሬታ ያላቸው ባለሆቴሎች ቅሬታቸውን ማቅረብና መስተናገድ እንደሚችሉ በተሰጠው እድል መሰረት በተወሰኑ ሆቴሎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመልከት ለመጨረሻ ጊዜ የትኛው ሆቴል ምን ደረጃ አገኘ የሚለውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል፡፡

Thursday, November 5, 2015

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያና የ2008 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻፀምን አስመልክቶ በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡



 በዕለቱም በርካታ በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን አዲስ ከተሾሙት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ከሆኑት ወ/ሮ መአዛ ገብረመድህን ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡
 በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፖሊሲ እቅድ ዝግጅት ባለሞያ የሆኑት አቶ ባህረዲን መንሱር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች፣ የዕትዕ አፈፃፀም በጥቅል ከባህል ልማት፣ ከቱሪዝም ገበያና ልማት አንፃር እና ሌሎች አበይት ተግባራት ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች የነበሩ ድክመቶችና ጠንካራ አፈፃፀሞች ላይ እንዲሁም የ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ምን ምን ዕቅዶች አካቷል የሚለውንና የ2008 በጀት ዓመት ዕቅድ የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል፡፡ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዙሪያ በአጠቃላይ የተከናወኑት ተግባራት ሲፈተሸ እና ሲገመገም የተሰራው ስራ የመጀመሪያው ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን እንደሚያሳይ ገልፀዋል፡፡

Saturday, October 10, 2015

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተሟላ ጥንተ-አፍሪካዊ ዘረ-መል/GENOME/ ተገኘ


በሀገራችን ደብቡ ክልል ጋሞ በተባለ መካነ-ቅርስ ከፍተኛ ስፍራ ሞጣ በሚባል ዋሻ እድሜው 4 500 ዓመት የሚገመትባይራየተሰኘ የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል ተገኘ፡፡
ከግኝቱ ላይ በጥንቃቄ በተወሰደ ናሙና በእፍሪካ በዕድሜ ከፍተኛ የሆነውን የዕድሜ ዘረ-መል አወቃቀር ማወቅ ተችሏል። የግኝቱን ስያሜ በተመለከት የጥናት ቡድኑ የተገኘበትን የጋሞ ማህበረሰብ ቋንቋ መሰረት ባደረገ ሁኔታ "ባይራ" ብሎ የሰየመው ሲሆን ትርጉሙም የበኩር ልጅ እንደማለት ነው።

Friday, October 2, 2015



የዓለም ቱሪዝም ቀን


ሃና መለሰ




አዲግራት የመስቀል በዓልን በድምቀት እያከበረች ነው፡፡




ሳውላ ጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል እያስተናገደች ነው፡፡


የደምባ ጎፋ ወረዳና የሳውላ ከተማ አስተዳደር በጋራ የሚያዘጋጁትና የጎፋ ብሔረሰብን የመስቀል በዓል አከባበር ምክንያት አድርጎ የተዘጋጀው የጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ 

Tuesday, September 8, 2015

ለመላው ኢትዮጵያውያን፣
በየትኛው የዓለም ጥግ ላላችሁ ወገኖቻችን፣
ለቱሪዝምና ባህል ልማቱ ዘረፍ ባለሙያዎችና ቤተሰቦችና
ለቱባ መጽሔት ደንበኞቻችን በሙሉ
ሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን ሃ/የተ/የግ/ማህበር መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ! ይጠብቃትም፤

Monday, August 31, 2015

መስቀልን በደምባ ጎፋ
ጎፋ ጋዜ ማስቃላ፤
ከመስከረም 9-10/2008 ዓ.ም.

በሳውላ ከተማ

አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፣ ባዛርና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው፡፡




የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሬክቶሬት፣የፋሽንና ዲዛይነሮች ማህበራትና ሜኖናይት ኢኮኖሚክ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን / MEDA/ በመተባበር የኢትዮጵያ ፋሽን አዲስ  ገልፅታ /New Images of Ethiopian Sustainable Fashion/ በሚል መሪ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የባህል ልብስ አምራቾች ፤ ዲዛይነሮች ሌሎች መሰል አካላት ባሳተፈ መልኩ አገር አቀፍ የፋሽን ትርት፤ ባዛርና አውደ ርዕይ ከነሐሴ 26 እስከ ነሐሴ 30 2007 ዓ.ም በኦሮሞ የባህል ማዕከል ይከናወናል፡፡


Wednesday, August 19, 2015

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስትጨርስ፤
ዓመታዊ የጎብኚዎቿን ቁጥር 2.16 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዳለች፡፡
በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ገቢ እያስገኘ መጥቷል፡፡ የፈረንጆቹ 2012 ዓመት 1 ቢሊዮን ያክል ጎብኚ የቱሪስት ፍሰት ተመዝግቦ 1.03 ትሪሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ በዚሁ ዓመት አፍሪካ ድርሻ 34 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ሀገራችን የመጀመሪያውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስታጠናቅቅ በ750 ሺ የውጪ ጎብኚዎች ተጎብኝታ ያገኘችው ገቢ 2 ቢሊየን ብር ደርሶ ነበር፡፡

Tuesday, August 18, 2015

የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ጋር በመሆን ከሚያዚያ 1ቀን 2007ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርት ላይ በኮኮብ ደረጃ የመመደብ ስራ የጀመረ ሲሆን በቅድሚያም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች ላይ የደረጃ ምደባ ስራው ተከናውኗል፡፡ በዚህም መሰረት በኮኮብ ደረጃ የመመደቡ ስራ ተጠናቆ ውጤቱ ነሐሴ 2,2007 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ ሆኗል፡፡ 

Wednesday, July 8, 2015



ኢትዮጵያ የ2015 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ፤
የአውሮፓ የቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት ኢትዮጵያን የባህላዊ ቱሪዝም መዳረሻ ብሎ መርጧታል፡፡ ይህው ካውንስል በ2015 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ በሚልም ነው የመረጣት፡፡ ይህን ሽልማት በማስመልከት የኢፊዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አሚን አብዱልቃድር ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ሰይድና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ታደሰ ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሽልማቱን በይፋ ሐምሌ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በብሔራዊ ቤተ መንግስት በሚደረግ ስነ ስርዓት እንደምንቀበል ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ለዙምባቤ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ዓመታዊ የዓለም የተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻነት ሽልማት በማግኘት ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን በዘንድሮው ሽልማት ከ31 በላይ ሀገራት ዕጩ ነበሩ፡፡ ይህንን ሽልማት በብሔራዊ ቤተ መንግስት በሚደረገው ስነ ስርዓት ስንቀበል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በአመራርነት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ልማት ላበረከቱት የላቀ የአመራርነት ሚና እውቅና የሚቸራቸው ይሆናል፡፡
ሽልማቱን ለመስጠት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው የአውሮፓ የቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት ቀናት ቆይታው በኢትዮጵያ የሚገኙ መዳረሻዎችንና ባህላዊ እሴቶችን የሚጎበኝ ይሆናል፡፡