Wednesday, May 2, 2012

ኮንሶ ካራት



konso karat

እንግዳ ተቀባዩ የኮንሶ ህዝብና
ዓለም በቅርስነት የመዘገበው የኮንሶ ባህላዊ መልከአ-ምድር


Artist Bersha  Bezuneh Tesfa
ራት ከአዲስ አበባ በ600 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፤ ከደቡብ ኦሞ ቀጠና ከተሞች አንዷና ደማቋ ስትሆን በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የምትገኘዋ ኮንሶ ወረዳ መዲና ናት፤ ካራት የንግድ እንቅስቃሴ ያለባት ደማቅ ከተማ ናት፤ ይህ ድምቀቷ በተለይም ሚያዝያ 20 ቀን 2004 ዓ.ም የተለየ ድባብ ነበረው፡፡

ዕለቱ የኮንሶ ህዝብ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ያከናውነው የነበረው አፍሪካዊ የግብርና ስራ ጥበብ እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዓለምን ትኩረት ስቦ አልፎም በዩኔስኮ ተመዝግቦ የዓለም ቅርስ የሆነበት ስኬት በማስመልከት በተመዘገበ በ295ኛው ቀን የተዘጋጀ የእውቅና አከባበር በዓል ነው፡፡ ብዙ የኮንሶ አባቶች ይህን ቀን እንመለከተዋለን ብለው አስበው እንደማያውቁ  ይናገራሉ፤ ለዚህም ነው ካራት ከተማ ከታሪኳ የማይጠፋን አንድ ብሄራዊ ኩነት ለማዘጋጀት የቻለችው፤
                                                                                                       ቀራጺ በርሻ ብዙነህ ተስፋ


እንደብዙ ታዳሚዎች ስሜት በዓሉን ያደመቀው የኮንሶዎች የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ነው፤ ለእንግዳ ያሳዩት የነበረው እንክብካቤ ካራት ካስተናገደችው ክስተት ጋር ተዳምሮ የኮንሶ ምድር ከታዳሚዎች አእምሮ እንዳይጠፋ አድርጎታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ፣የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ካሳ ተ/ብረሃን የፍትህ ሚንስትሩ ክቡር አቶ ብረሃነ ሃይለ፣ ክቡር አቶ አሚን አብዱልቃድር፣ክብርት ወ/ሮ ታደለች ዳላቾ፣ ክቡር አቶ ሙሃሙዳ አህመድ ገአስ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣የክልልና የዞን አመራሮችና ምሁራን በእንግድነት የተገኙበት ይህ ዝግጅት በእንድ ቀን ግዜ ውስጥ አያሌ ተግባራትን አካቶ በስኬት የተከናወነ ነበር፡፡

ኮንሶ ካራት
Konso Karat
konso karat square/ኮንሶ ካራት
የኮንሶ ባህላዊ መልከአ-ምድር በዓለም የቅርስ መዝገብ መመዝገቡን የሚገልጸው እና በኮንሶ የእርከን ጥበብ ተምሳሌት በተገነባው አደባባይ ላይ የቆመው የዩኔስኮ አርማ አናቱ ላይ የኮንሶን ህዝብ አንድ አድርጎ የሚወክለው ማረሻ ተሰቅሎበታል፡፡ በአደባባዩ የቆሙት ዘጠኝ መብራቶች ዘጠኙን የኮንሶ ጎሳዎች ይወክላሉ፤ ዘጠኙ እኩል በመሆናቸው በኮንሶ ጎሳዎች መካከል ያለውን አለመበላለጥ ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ዘጠኙን ክልሎች ይወክላሉ፤ ዘጠኝ በኮንሶ ህዝብ ዘንድ ትርጉም ያለው ቁጥር ነው፡፡ ይህንን ድንቅ ስራ ቀራጺ በርሻ ብዙነህ ተስፋ ሰርቶታል፡፡ ኮንሶዎች የቀራጺውን ታታሪነት በመመልከት ጥበቡን በማድነቅ፣ ማህበረሰቡን መምሰሉን በማወደስ በርሻ የሚለውን ስም አጎናጽፈውታል፡፡ ስሙን ያስረከቡት የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌሌቦ  ናቸው፡፡ የስያሜው ትርጓሜ ብረሃን፣ያነጋ፣ንጋት እንደማለት ነው፡፡

የአደባባይና የአርማ ምርቃት፣የኮንሶ አምባ መንደሮች ጉብኝትና የኮንሶ ሙዚየም እና የባህል ማእከል ጉብኝትን ያካተተው ዝግጅት፣ሰኞ ስለ ኮንሶ ቋንቋ እና የፊደል ገበታ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡


No comments:

Post a Comment