Tuesday, May 29, 2012



የአቡኑ ከተማ

በሰሜን ሸዋ ዞን .. ከደጋማው የመንዝ ምድር .. ተፈጥሮው በብዙ ከሚተርክበት .. መልከአ-ምድር መሃል በዚያ ንጹህ አየር በሚሳብበት ውብ ምድር የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡

ሰላድንጋይ የዚህ ድንቅ ስፍራ መጠሪያ ነው፡፡ ከሰሜን ሸዋ ዞን መዲና ከደብረ ብርሃን ከተማ በ75 ከ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሰላ ድንጋይ ኢትዮጵያን ለ38 ዓመታት በፓትሪያሪክነት ያገለገሉት አባት የአቡነ ማቴዎስ የመንበር ጵጵስናቸው መቀመጫ ነበረች፡፡

 ግብጻዊው ፓትሪያሪክ አቡነ ማቴዎስ በዚሁ ስፍራ በ1875 ዓ.ም የማርቆስ ቤተ-ክርስቲያንን አሰርተዋል፡፡

Thursday, May 17, 2012


የሥነ-ጽሁፍ ሃብቶቻችን የቅርስነት ዋጋቸው….. በዜጎች ተመዝኖ ይሆን

ብራና
ቅርስ የአንድ ህዝብ ማንነት ነው፤ ከቅርሱ ጀርባ የቅርሱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ፣እሴቶችና መገለጫዎቹ አሉ፡፡ ለዚህም ነው ቅርሶች ባለቤታቸው ከሆኑ ህዝቦች ህልውና ተለይተው የማይታዩት፡፡ ከቅርስ ጋር ተያይዞ በሃገራችን ያለው አስተሳሰብ ቅርስን ከሥነ-ህንጻ ጥበብ ጋር ብቻ በማቆራኘት የመፈረጁ ባህል ከዘርፍ ጋር በቂ ግንዛቤ በሌላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ባለሙያም በሆኑ አካላት ጭምር እየተስተዋለ ነው፤ ለዚህም ነው የጽሁፍ ቅርሶቻችን ስንል ስለ ጽሁፍ ሃብቶቻችንና ስለ ቅርስነት ይዘታቸው ማንሳት የፈለግንው፤

Sunday, May 13, 2012

calander/
ባሕረ-ሐሳብ በአለቃ ያሬድ ፈንታ


በስልጤ ህዝብ ባህል ዙሪያ ለዓመታት ተጠንቶ የተዘጋጀው የኬይረዲን ተዘራ መጸሐፍ ለህትመት በቃ፡፡
መጸሀፍ ዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ባህል ማእከል በታላቅ ድምቀት ተመርቋል፡፡

ወጣቱ ኬይረዲን ተዘራ ግዜ ወስዶ፣ታሪክ አዋቂ የስልጤ ሽማግሌዎችን ቃለ-መጠይቅ አድርጎ፣በርካታ መዛግብትን አገላብጦ…ያዘጋጀው ይህ መጸሐፍ የብሄረሰቡን ባህልና ታሪክ በማስተዋወቅ ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ብዙዎች ተንብየዋል፡፡ ኬይረዲን በተለያዩ ግዜያት በወራቤ ከተማ ይደረጉ በነበሩ የቋንቋ፣ባህልና ታሪክ ሲምፖዚየሞች ያቀርባቸው የነበሩ ጥናቶች የስልጤ ሽማግሌዎችን በመማረክ ለምርቃት አብቅተውታል፡፡

Monday, May 7, 2012


የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች

የሃገርህን እወቅ ክበብ የሶስት ቀናት ጉዞ

እውቀት ከራስ ይጀምራል፣


ባህልና ቱሪዝም
ልኡኩ ሲንቀሳቀስ
የሃገር ውስጥ ቱሪዝም እንደቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዘርፍነት ብቻ የሚታይ አይደደለም፣ ጠቀሜታዎቹ በርካታ ናቸው፣ በተለይም ዜጎች ለሃገራቸው ቅርስ፣ባህልና እሴት መጠበቅ መልማትና መተዋወቅ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ቁልፉ መንገድ የሃገር ውስጥ ቱሪዝምን ማስፋፋት ነው፡፡

ወደ ራሱ ጓዳ ብዙም ሳይሳካለት የኖረው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ በተቃራኒው ለሃገር ውስጥ ቱሪዝም መስፋፋት ሲያደርግ በነበረው ጥረት በርካታ መስሪያ ቤቶች ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ ጉብኝት እንዲያደርጉ ያስቻሉ የሃገርህን እወቅ ክበባት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ ይህም ሆኖ ብዙዎች ላይ ጥያቄ የፈጠረው የራሱ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች የሃገርህን እወቅ ክበብ መቼ ይሆን ሃገሩን ለማወቅ እግሩን የሚያነሳው የሚለው ነበር፡፡

Wednesday, May 2, 2012

ኮንሶ ካራት



konso karat

እንግዳ ተቀባዩ የኮንሶ ህዝብና
ዓለም በቅርስነት የመዘገበው የኮንሶ ባህላዊ መልከአ-ምድር


Artist Bersha  Bezuneh Tesfa
ራት ከአዲስ አበባ በ600 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፤ ከደቡብ ኦሞ ቀጠና ከተሞች አንዷና ደማቋ ስትሆን በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የምትገኘዋ ኮንሶ ወረዳ መዲና ናት፤ ካራት የንግድ እንቅስቃሴ ያለባት ደማቅ ከተማ ናት፤ ይህ ድምቀቷ በተለይም ሚያዝያ 20 ቀን 2004 ዓ.ም የተለየ ድባብ ነበረው፡፡

ዕለቱ የኮንሶ ህዝብ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ያከናውነው የነበረው አፍሪካዊ የግብርና ስራ ጥበብ እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዓለምን ትኩረት ስቦ አልፎም በዩኔስኮ ተመዝግቦ የዓለም ቅርስ የሆነበት ስኬት በማስመልከት በተመዘገበ በ295ኛው ቀን የተዘጋጀ የእውቅና አከባበር በዓል ነው፡፡ ብዙ የኮንሶ አባቶች ይህን ቀን እንመለከተዋለን ብለው አስበው እንደማያውቁ  ይናገራሉ፤ ለዚህም ነው ካራት ከተማ ከታሪኳ የማይጠፋን አንድ ብሄራዊ ኩነት ለማዘጋጀት የቻለችው፤
                                                                                                       ቀራጺ በርሻ ብዙነህ ተስፋ