Sunday, August 12, 2018


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በሀገረ ሰብ የባህል ሕክምና ዙሪያ ሀገራዊ የውይይት መድረክ አዘጋጀ፡፡
የባህል መድኃኒት ጠበብቶች እና ሳይንሳዊ ሊቃውንቶች ተቀራርቦ መስራት ላይ ችግር እንዳለባቸው ተገልጾዋል፡፡
*******


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አምስት ኪሎ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ በሀገረሰባዊ ሕክምና ዙሪያ ሀገራዊ ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱ ሀገረሰባዊ የህክምና ጥበባችን ከየት? ወደየት? በሚል መነሻ የቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መድሃኒት መምህራን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

Tuesday, May 29, 2018


የትግራይ የባህል ፌስቲቫል በአክሱም ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በሜሮን ታምሩ

በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙ 53 ወረዳዎች ውስጥ 34ቱ ወረዳዎች የተሳተፉበት ክልል አቀፍ የባህል ሳምንት በስልጣኔ ፈር ቀዳጅ በሆነችው በአክሱም ከተማ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ 

Saturday, February 3, 2018

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር 78ተኛ ዓመታዊ የፈረስ ትርዒት ነገ ይካሄዳል፡፡


በአዊ ብሔረሰብ ዞን በየዓመቱ የሚከበረውና በሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማህበር የሚዘጋጀው ዓመታዊ የፈረስ ትርዒት ዘንድሮ ለ 78ተኛ ጊዜ ነገ ጥር 27 2010 ዓ.ም. በእንጅባራ ከተማ በድምቀት ይካሔዳል፡፡


በ 1933 ዓ.ም. በአደዋ ጦርነት የዘመተውን የፈረሰኛው ጊዮርጊስ ታቦትና የፈረሰኛ አርበኞችን ተጋድሎ ለመዘከር በኢጣሊያ ወረራ ወቅት የተፀነሰው የአዊ ፈረሰኞች ማህበር ለ 78 ተከታታይ ዓመታት ባህላዊ የፈረስ ትርዒት ሲያዘጋጅ ቆይቷል ዘንድሮም የአማራ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከፌደራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ባለድርሻ አካላት በመተባበር የደገፉት ይህ በዓል በአዊ ብሔረሰብ ዞን ዋና ከተማ እንጅባራ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

Friday, October 6, 2017



የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል /ሄቦ/


በየም ብሔረሰብ ልዩ ስፍራ ከሚሰጣቸው ባህላዊ በዓላት አንዱ ሄቦ ነው፡፡ በጉጉት የሚጠበቅና ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎበት የሚከበረው የሄቦ በዓል የተጀመረበት ትክክለኛ ጊዜ ባይታወቅም ከጥንት ጀምሮ የብሔረሰቡ ዘመን መለወጫ በዓል ሆኖ  ሲከበር የመጣ በዓል ነው፡፡



የየም ልዩ ወረዳ አስናቂ መስህቦች

አንገሪ ቤተ መንግስት

የየም ልዩ ወረዳ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ በ239 ኪሎ ሜትር ከክልሉ መቀመጫ ከሐዋሳ በቡታጅራ በኩል 333 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳውን በደቡብ ኦሮሚያ ክልልና ሀዲያ ዞን በሰሜን ኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞንና ሀዲያ ዞን፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 56 ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነው የየም ብሔረሰብ በዋናነት የሚኖረው በየም ልዩ ወረዳ ክልል ውስጥ ሲሆን ከወረዳው ውጭ በጅማ ዞንና በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በብዛት ይኖራሉ፡፡   

Friday, March 3, 2017

121ኛው የአድዋ ድል በዓል በብሄራዊ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ በአድዋ ከተማ ተከብሯል፡፡








121ኛው የአድዋ ድል በዓል በብሄራዊ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ በአድዋ ከተማ ተከብሯል፡፡ የአድዋ 121 የድል በዓል በአድዋ ከተማ ጦርነቱ በተከናወነበት የሶሎዳ ተራራ ግርጌ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ ‹‹ የአድዋ ድል ብዝኃነን ላከበረቻት  ኢትዮጵያ ድህነትን ለማሸነፍ የሚያስችል ህያው አብነት ነው››!! በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡