Wednesday, October 2, 2013

meet ethiopian in gondar

Meet Ethiopian In Gondar

ደቡብ ኦሞ እና መስህቦቿ


south omo Ethiopia
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ውስጥ ከተዋቀሩት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሰሜን ጋሞጎፋ ከፋ ዞኖች እና ደቡብ ኦሞ ዞን የኮንታ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ቤንችማጂ ዞንና ሱዳን፣ በምስራቅ ኮንሶ ልዩ ወረዳ እና በደቡብ ደግሞ ከኬንያ ትዋሰናለች፡፡ ከአ/አበባ በ755 ኪ.ሜ እና ከክልሉ መዲና አዋሣ በ525 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ደቡብ ኦሞ ዞን 23530 ስኩየር ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ሲኖራት በስምንት ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አሰተዳደር የተዋቀረ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ ነው፡፡ በከፊል የአየር ንብረቱ ቆላማ ሲሆን ከ360-3300 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ያላቸው መሬቶችም አሉ፡፡

መስቀልን በደንባ ጎፋ


Gofa
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በጋሞ ጎፋ ዞን በደምባ ጎፋ ወረዳ ተገኝተናል፡፡ ወረዳዋ ከመዲናችን አዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ516 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ወረዳዋን በስተ ምስራቅ የዛላ ወረዳ፣ በደቡብ የገዜ ጎፋና ኦይዳ ወረዳዎች፣ በምዕራብ የመሎ ኮዛ እና በሰሜን የቁጫ ወረዳና የዳውሮ ዞን ያዋስኗታል፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋት 97,900 ሄክታር ሲሆን በ38 ቀበሌያት የተዋቀረ ነው፡፡ የወረዳው አጠቃላይ ህዝብ ብዛት 150,000 የደረሰ ሲሆን የራሱ የሆነ የቋንቋና የባህል እሴቶች ባለቤት ናት፡፡

ወረታ እንደ ቱሪስት መዳረሻ



werta city
ለምለሙ የፎገራ ምድር የምርታማነት ቀጠና ነው፡፡ ትርፍ አምራች በሆነው ምድር የተከበበችው ወረታ ከተማ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ከባህር ዳር ጎንደር በሚወስደው ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡

ወረታ ከአዲስ አበባ ኪሎ ሜትር ከክልሉ ርእሰ ከተማ ከባህር ዳር በ55 ኪሎ ሜትር፣ ከጎንደር ከተማ 120 ኪሎ ሜትር፣ ከደብረ ታቦር ከተማ ደግሞ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ 14,097 ወንድ እና 14,379 ሴት በድምሩ 28,475 ህዝብ የሚኖርባት ወረታ በ1942 ዓ.ም ገደማ ነበር የተቆረቆረችው፡፡ ይሁን እንጂ ፈጣን ልማቷን ተከትሎ በሚሊኒየሙ ማለትም በ2000 ዓ.ም በከተማ አስተዳደርነት ተደራጀች፡፡

የሀላባ ልዩ ወረዳ የቱሪስት መዳረሻዎች


የሀላባ ልዩ ወረዳ በክልላችን  ካሉ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ከሚገኙባቸው ልዩ ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ በሀላባ ልዩ ወረዳ የተለያዩ ሰው ሰራሽ፣ ታሪካዊ እና የተፈጥሮ ቅርሶች ተከማችተው ይገኙበታል፡፡ እነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል የአርቶ ፍል ውሃ፣ የስፋሜ ዋሻ፣ የኑርአህመድ መካነ-መቃብር፣ የብላቴ ፏፏቴ/ፋማ/ ፓርክ፣ የአሶሬ ደን እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች የውጭ ምንዛሬ ከማምጣታቸውም በላይ ለተለያዩ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የቻሉ በመሆናቸው አሁንም በእነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ቦታው ክፍት መሆኑን በመጠቆም ነው፡፡