Friday, October 6, 2017



የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል /ሄቦ/


በየም ብሔረሰብ ልዩ ስፍራ ከሚሰጣቸው ባህላዊ በዓላት አንዱ ሄቦ ነው፡፡ በጉጉት የሚጠበቅና ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎበት የሚከበረው የሄቦ በዓል የተጀመረበት ትክክለኛ ጊዜ ባይታወቅም ከጥንት ጀምሮ የብሔረሰቡ ዘመን መለወጫ በዓል ሆኖ  ሲከበር የመጣ በዓል ነው፡፡



የየም ልዩ ወረዳ አስናቂ መስህቦች

አንገሪ ቤተ መንግስት

የየም ልዩ ወረዳ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ በ239 ኪሎ ሜትር ከክልሉ መቀመጫ ከሐዋሳ በቡታጅራ በኩል 333 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳውን በደቡብ ኦሮሚያ ክልልና ሀዲያ ዞን በሰሜን ኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞንና ሀዲያ ዞን፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 56 ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነው የየም ብሔረሰብ በዋናነት የሚኖረው በየም ልዩ ወረዳ ክልል ውስጥ ሲሆን ከወረዳው ውጭ በጅማ ዞንና በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በብዛት ይኖራሉ፡፡