Sunday, June 24, 2012


በመሰሮ ኢበሌን በሰሮ

እንደ ስልጤ ያያም ኢልቅ/ የዘመን አቆጣጠር/ መሰሮ 1/ ሰኔ 20/

 የስልጤ የዘማን ኢጋኘ አያም/ዘመን መለወጫ

ያያም ኢልቅ ይሉታል የቀን አቀማመር ስልት ዘዴአቸውን፡፡ በደቡብ ክልል የሚገኙት ስልጤዎች የራሳቸው የቀን አቀማመር ካላቸው የሃገራችን ህዝብ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ወቅት የዓመቱ የመጨረሻ ወር ነው እንደ ስልጤዎች የቀን አቀማመር ሰኔ 20 ዓዲስ አመታቸው ነው፡፡ መሰሮ 1 ይሉታል እነሱ፡፡ ዘንድሮም በእለተ አርጴ/ረዕቡ/ ሰኔ 20 የሚውለው የስልጤ የዘመን መለወጫ ለስልጤዎች አዲስ አመታቸው ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በዘመን አቆጣጠሩ ላይ የሚደረጉ ጥናቶች የተጀመሩ ሲሆን የዘመን ቀመሩ መነሻ..መሰረት ያደረጋቸው ዋና ዋና መገለጫዎችና ሌሎች ሚስጥራቱ  ዙሪያ ካተኮሩት ጥናቶች በመነሳት ስለ አቀማመሩ ሰፊ መረጃ ይገኛል የሚል እምነት አለ፡፡




                                                           ለመላው የስልጤ ህዝብ ሀበይ ለሀጂሲ ዘማን በወገሬት አጄጄሙ! ብለናል

Tuesday, June 19, 2012


ብሄራዊ የቱሪዝም መማክርት ጉባኤ ውይይቱን አካሄደ

ወቅታዊ ጉዳዮች ተነስተዋል፤

የቱሪዝም ሥነ-ምግባር መምሪያው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ዜና፡- ሀሚኮ

ትናንት ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ሙሉ ቀን በአዲሱ ራንድ ሰን ብሉ ሆቴል የተካሄደው የብሄራዊ የቱሪዝም መማክርት ጉባኤ በዋናነት በዓለም ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀውንና የሃገራችን ቱሪዝም አጠቃላይ ጠቀሜታዊ ይዘት ላይ ያተኮረው የጥናት ጥቅል ውጤት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

Friday, June 15, 2012

አሁን አየ ዓይኔ     
የቱሪዝም ንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ
የሃገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለዘመናት ይጓዝበት ከነበረው ከርፋፋና ቀርፋፋ አካሄድ ወጥቶ ያለፍትን ጥቂት ዓመታት ሶምሶማ ወደሚባል ፍጥነት እየገባ መጥቷል፡፡ የሁልም ጊዜም ቁጭታችን ባለን ነገር ባለመጠቀም ከሌላቸው ህዝቦች ውራ ቁጥር መግባታችን ነበር፡፡ ስለአለን ነገር እንኳን ስናስብ ከሌላው የምንልቅበት በርካታ ነገር አለ፤ እኛ ያለን ሃብት እውቀት ገንዘብና ቴክኖሎጂ ሊያመጡት አይችሉም፤ ብዝኃ- ህይወትን ከባህል ጋር፣ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ሃብቶችን ታድለናል፡፡ ለጥቁር ህዝብ ተምሳሌት የሚሆን ትናንትና ያለን ህዝቦች ነን፤ ይህንን ተጠቅመን መጠቀም አቅቶን ኑሯል፤ እንደውም አናወራውም ስለራስ ማውራት መታበይ ነው የሚል ብሂል አለን፤ ስለራስ ካልተወራ ውጤት የማይገኝበት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ልባችንን የምናሳርፍበት አልሆን ያለውም ለዚህ ነው፡፡

Thursday, June 7, 2012


                                       ራስ ግንብ
ይህ ቤተመንግስት የተገነባው በከፍታ ቦታ ላይ ሲሆን ከፋሲል ቤተ-መንግስት በስተሰሜን በኩል 300 ሜትር ርቀት ላይ ነው፡፡  ይህ ቤተመንግስት ባለሁለት ፎቅ ሆኖ ከመሰረቱ ሰፊና ወፍራም ግንባታ ያለው ሲሆን ወደላይ እየቀጠነ የሚሄድ ነው፡፡

ሁለት ወታደሮች (ማማዎች) ሲኖሩት ሶስተኛው ግን በባለ አራት ማዕዘን ማማው መሐል ይገኛል፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የአሰራር ስልቶች በዘመኑ ሰቀላ ግንብ ወይም ከበሮ ግንብ በመባል ታወቃሉ፡፡ በተለይ አራተኛውና ትልቁ ማማ (Tower) ይህ ቤተመንግስት ግርማ ሞገሱ የበለጠ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ ይህ ሁሉ ውበትና የአሰራር ጥበብ የፈሰሰበት ቢሆንም  ከአፄ  ፋሲል  ቤተመንግስት (ግንብ) በመጠኑ ያነሰነው፡፡ ነገር ግን በቅርጹና በአሰራር ጥበቡ ተመሳሳይነት አለው፡፡

                  ራስ ግንብ  ሙዚየም
               RAS GENB MUSUME

Tuesday, June 5, 2012

                 አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም
                                              ሙዚየም ተመረቀ
አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ባስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም የተሠራው አዲስ ሙዚየም ግንቦት 18 ቀን 2004 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡
በትግራይ ክልል በዓድዋ ወረዳ የሚገኘውና ከገዳሙ እኩል ዕድሜ 1500 ዓመታትን ያስቆጠረ የወንጌል መጻሕፍትና ጥንታውያን ቅርሶች ላሉበት ገዳም ዘመናዊ ሙዚየሙ የተገነባለት ከ400 ሺሕ ብር በላይ ወጪ ነው፡፡

መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቱያን የቅርስ ጥበቃና ምዝገባ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምርያ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፈረንሣይ መንግሥት በሰጠው ከ400 ሺሕ ብር በላይ ዕርዳታ መሠረት ጥንታዊው ሕንፃ ታድሶና ተዘጋጅቶ ለቤተ መዘክር አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡

Monday, June 4, 2012


ሰኔ ሰላሳ የሚያሳድዳቸው የባህል ፌስቲቫሎች

ደማቁ የእሬቻ በዓል
ይሄ ሰኔ ሰላሳ የሰነፍ ተማሪ  የምጥ ቀን ነበር…አሁን አሁን ተቋማት.. በጀት ዓመታቸውን ለመጨረስ…ከፋይዳው ይልቅ ለሪፖርት የሚሆን ተግባር ለማከናወን ተገልጦ የሚታይ ጉድ እየተመለከትን ነው፡፡ የባህል ፌስቲቫሎች በባህል ልማት በቱሪዝም ምርትነትና በገጽታ ግንባታ፤ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንንም በእጅጉ እናበረታታለን፤ ከዳር ዳር የባህል ፌስቲቫሎች እንዲናኙ ምኞት ብቻ ሳይሆን ይፈጸም ዘንድ እንተጋለን፤ግን እንዴት ? ዓላማስ አለው ወይ…ግቡስ ምንድን ነው እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች ሊመልስ ይገባዋል፡፡