Tuesday, June 19, 2012


ብሄራዊ የቱሪዝም መማክርት ጉባኤ ውይይቱን አካሄደ

ወቅታዊ ጉዳዮች ተነስተዋል፤

የቱሪዝም ሥነ-ምግባር መምሪያው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ዜና፡- ሀሚኮ

ትናንት ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ሙሉ ቀን በአዲሱ ራንድ ሰን ብሉ ሆቴል የተካሄደው የብሄራዊ የቱሪዝም መማክርት ጉባኤ በዋናነት በዓለም ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀውንና የሃገራችን ቱሪዝም አጠቃላይ ጠቀሜታዊ ይዘት ላይ ያተኮረው የጥናት ጥቅል ውጤት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡


የመማክርቱን ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ በንግግራቸው ላይ"የኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ ላይ ከተቀመጡት የፖሊሲ ጉዳዮች አንዱ በቱሪዝም ልማት ውስጥ የሚሳተፍ ተዋናዮች መካከል ትብብራዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተለይቷል፡፡" ብለዋል፡፡

 የክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች፣ የእምነት ተቋማት፣ የሆቴል አሰሪ ማህበር፣የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር፣የኢትዮጵያ ቱር ኦፕሬተር ማህበር፣የአዲስ አበባ ቱር ኦፕሬተር ማህበር፣ ንግድ፣ገንዘብ፣ትምህርት፣ኢንዱስትሪና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አባል የሆኑበት ጉባኤ በዚህ ቀን በቱሪዝም ሥነ-ምግባር መመሪያው ላይም ውይይት አድርጓል፡፡

ለረጅም ግዜ ክፍተት ሆኖ የኖረውን የሥነ-ምግባር መመሪያ በማውጣት ረገድ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር መሆኑን በመጥቀስ ቢጨመሩ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ግብአቶች የጉባኤው አባላት ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment