Tuesday, November 17, 2015


ድሬደዋ በሀገር ደረጃ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን እያስተናገደች ነው፡፡





እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንሳና ባህል ድርጅት በወሰነው መሰረት በየዓመቱ ኖቨምበር 16 ቀን የዓለም የመቻቻል ቀን ሆኖ በአባላ ሀገራቱ ይከበራል፡፡ አባል ሀገራቱም በዓሉን በተለያየ መልኩ ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡ ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህንን በዓል ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ከህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆይ ዝግጅት እያከበረችው ነው፡፡

Saturday, November 7, 2015

የሆቴሎች ኮከብ ደረጃ ምደባ ይፋ ሆነ



የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባሩት መንግስታት የዓለም ቱሪስት ድርጅት ጋር በመሆን ከሚያዚያ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርቶችን በኮኮብ ደረጃ የመመደብ ስራ የጀመረና በቅድሚያም የአዲስ አበባ ከተማ ሆቴሎች ጊዜያዊ የደረጃ ምደባ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

   ከጊዜያዊ የደረጃ ምደባው በኋላ በምደባው ቅሬታ ያላቸው ባለሆቴሎች ቅሬታቸውን ማቅረብና መስተናገድ እንደሚችሉ በተሰጠው እድል መሰረት በተወሰኑ ሆቴሎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመልከት ለመጨረሻ ጊዜ የትኛው ሆቴል ምን ደረጃ አገኘ የሚለውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል፡፡

Thursday, November 5, 2015

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያና የ2008 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻፀምን አስመልክቶ በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡



 በዕለቱም በርካታ በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን አዲስ ከተሾሙት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ከሆኑት ወ/ሮ መአዛ ገብረመድህን ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡
 በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፖሊሲ እቅድ ዝግጅት ባለሞያ የሆኑት አቶ ባህረዲን መንሱር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች፣ የዕትዕ አፈፃፀም በጥቅል ከባህል ልማት፣ ከቱሪዝም ገበያና ልማት አንፃር እና ሌሎች አበይት ተግባራት ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች የነበሩ ድክመቶችና ጠንካራ አፈፃፀሞች ላይ እንዲሁም የ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ምን ምን ዕቅዶች አካቷል የሚለውንና የ2008 በጀት ዓመት ዕቅድ የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል፡፡ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዙሪያ በአጠቃላይ የተከናወኑት ተግባራት ሲፈተሸ እና ሲገመገም የተሰራው ስራ የመጀመሪያው ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን እንደሚያሳይ ገልፀዋል፡፡