Friday, October 6, 2017



የየም ልዩ ወረዳ አስናቂ መስህቦች

አንገሪ ቤተ መንግስት

የየም ልዩ ወረዳ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ በ239 ኪሎ ሜትር ከክልሉ መቀመጫ ከሐዋሳ በቡታጅራ በኩል 333 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳውን በደቡብ ኦሮሚያ ክልልና ሀዲያ ዞን በሰሜን ኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞንና ሀዲያ ዞን፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 56 ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነው የየም ብሔረሰብ በዋናነት የሚኖረው በየም ልዩ ወረዳ ክልል ውስጥ ሲሆን ከወረዳው ውጭ በጅማ ዞንና በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በብዛት ይኖራሉ፡፡   


ልዩ ወረዳው በ31 የገጠርና 4 የከተማ ማዘጋጃ ቤት ቀበሌዎች የተደራጀ ነዉ፡፡ የልዩ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ሳጃ ነው፡፡ ከተማውን ከአዲስ አበባ ጅማ በሚወስደው ዋና የአስፋልት መንገድ የሚያቋርጠው ሲሆን ለግብርና፣ ለንግድና ለሆቴል ኢንቨስትመንት ምቹና የተሟላ መሠረተ ልማት ያለው ነው፡፡
የልዩ ወረዳው የቆዳ ስፋት 742.5 ስኩዬር ኪሎ ሜትር  ነው፡፡ የወረዳው ህዝብ ብዛት በ1999 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት 80,647 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ማለትም በ2009 ዓ.ም. የወረዳው ህዝብ ብዛት ወንድ 54,489 ሴት 54,034 በድምሩ 108,524 መድረሱን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ትንበያ መረጃ ያሳያል፡፡ የየም ብሔረሰብ ራሱን የም ወይም የማ ብሎ ይጠራል፡፡ የሚጠቀምበትም ቋንቋ የምሳ ይባላል፡፡
ከ89.6 በመቶ በላይ የሚሆነው የልዩ ወረዳው ህዝብ በግብርና የሚተዳደር ሲሆን እንደ ገብስ፣ ጤፍ፣ስንዴ፣ በቆሎ፣  ያሉና የተለያዩ የአገዳና የመኽር ሰብሎች ፣ ፍራፍሬ እና አትክልት በሰፊው ይመረታል፡፡
የልዩ ወረዳው መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ ተራራማና ኮረብታማ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ 930 እስከ 2939 ሜትር ከፍታ ያላቸው አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡ የአየር ንብረ ደጋ 16 በመቶ፣ወይናደጋ 73 በመቶ እና ቆላ 11 በመቶነው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ801-1400 ሚሊ ሜትርና ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኑ ከ12-30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መካከል ነው፡፡የመሬት አቀማመጡ 20 በመቶ ተራራማ 3 በመቶ ሜዳ 12 በመቶ ደግሞ ተዳፋትሲሆን ቀሪው 65 በመቶ ኮረብታማ፣ ሰንሰለታማና ወጣገብ የሆነ ቶፖግራፊን የያዘ ነው፡፡የአፈሩዓይነት ቡናማ 25 በመቶ ቀይ አፈር 60 በመቶቀሪው 15 በመቶ ደግሞ ጥቁር አፈር እንደሆነ ይገመታል፡፡
የየም ልዩ ወረዳ ቱሪስት መስህቦች
ጥንታዊ የአንገሪ ቤተ መንግ
የየም ብሔረሰብ የራሱን የአስተዳደር መዋቅር መስርቶ በንጉሡ /ታቶ/ይተዳደር ነበር፡፡ ህዝቡሶስትሥርወ መንግታት ተፈራርቀው አስተዳድረውታል፡፡ የመጀመሪያው የጋማሥርወ መንግሥት ማዕከላዊ መቀመጫውን ዝማር-ማ /ኦያ አካባቢ/ በሚባል ስፍራ በማድረግሁለተኛው የጌሜሎሥርወ መንግሥት የሥርወ መንግሥቱን ማዕከላዊ መቀመጫ ካንፎቻ/ፎፋ መድኃኒዓለምቤ/ክርስቲያን በስተጀርባ/ እና የሞዋርወመንግ ማዕከላዊ መቀመጫውን አንገሪ በማድረግ ብሔረሰቡን አስተዳድረዋል፡፡ የአንገሪ ቤተ መንግት ከ13ኛውክፍለ ዘመን 2ኛ አጋማሽ አንስቶ የየም ግዛት በማዕከላዊ ግዛትውስጥ እስገባ ድረስ የሞዋ ርወ መንግት መቀመጫና መናገሻ በመሆን አገልግ፡፡


ቤተ መንግሥቱ ከልዩ ወረዳ ርዕሰ ከተማ ሳጃ 27.8 ኪሎ ሜትር በደቡባዊ ምስራቅ አቅጣጫ በጎሩምና አንገሪ ቀበሌ ሲገኝዛሬም ድረስ በስፍራው የሚገኙት በርካታ ታሪካዊ ሥነ-ሥርዓትና ክንዋኔዎች የተፈፀመባቸው ቦታዎች እንዲሁም ግርማ ሞገስ ያላቸው እድሜን ያስቆጠሩ አገር በቀል ዛፎች ለጥንታዊነቱ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡
የፎፋ ደብረ መድኒት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን

ፎፋ ደብረ መድሃኒት መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን

ጥንታዊ በሆኑ ሀገር በቀልና ከባህር ማዶ በመጡ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተከበበው የፎፋ ደብረ መድኒት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከልዩ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ሳጃ በ26 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በፎፋ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ በ1888 ዓ.ም. በየም ብሔረሰብ ሶስተኛው ሥርወ-መንግሥት ንጉስ በሆኑትጌራኖ (ፈታውራሪ ገ/መድህን) ዘመን እንደተቋቋመ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በአካባቢው ባለሙያዎች ጥበብ በቀለማት የተቀለሙ ከእሽኮኮና ከፍየል ቆዳ ተፍቀው የተዘጋጁ የተለያዩ የብራና ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ጥንታዊ አልባሳት እና ከእንጨት፣ ከእምነ-በረድና ከነሐስ የተሰሩ መስቀሎች ይገኙበታል፡፡
የብርብርሳ  ፏፏቴ

ብርብርሳ

ከአዲስ አበባ ጅማ በሚወስደው ዋና መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ በልዩ ወረዳው ዋና ከተማ ሳጃ ውስጥየሚገኘው የብርብርሳ ፏፏቴ መጠሪያውን ያገኘውዛቤ በመባል የሚጠራ ወንወደ ፏፏቴ ተቀይሮ መፍሰ በሚጀርበት ቦታ ላይ በሚገኝ ዛፍ ስም ሲሆን ዛፉ በእርና ምክንያት መውደቁን የአባቢው ነዋዎች ይናገራሉ፡፡የብርብርሳ ፏፏቴ ከትግርቀበሌ መንጭቶ የሚነሳ የምንጭ ውሃና የዛቤ ወንዝ ውህድ ነው፡፡ከፏፏቴው ጀርባ በተወሰነ ቁመት እና ውፍረት የተደረደሩት በሰው እጅ የተጠረቡ እንጂ ተፈጥሮ ያበጀቻቸው የማይመስሉት ዐለቶች እንዲሁም ፏፏቴውን ያጀቡት ቋጥኞች የፏፏቴውን ውበት አጉልተውታል፡፡
ዞፍካር ትክል ድንጋይ
ዞፍካር ትክል ድንጋይ በቀድሞው የልዩ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ፎፋውስጥ ከአሁኑ የልዩ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ሳጃ በ26.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ መስህብ ነው፡፡በስፍራውላይ ከ1888 ዓ.ም. በፊት በብሔረሰቡ ዘንድ በዘመኑ ታላላቅና ታዋቂ የሚባሉት የዕምነት ተቋማት ከመፈጠራቸውአስቀድሞቀብር ይፈፀምበት ነበር፡፡ በወቅቱም እንደ ሐውልት ይመለኩ እንደነበር እንዲሁም በቦታው ላይ በብዛት ይቀበሩ የነበሩት የሞዋ ጎሳዎች ቢሆኑም ሌሎችም በዚህ ስፍራ ይቀበሩ እንደነበር ይነገራል፡፡በዚህ ስፍራ ላይ ከሚገኙ ትክል ድንጋዮች መካከልበቁመት ትል 2.63 ሜትር የሚረዝም ሲሆን ትንሹ 51 ሴንቲ ትርቁመት አለው፡፡ በአጠቃላይ  በስፍራው ከ211 በላይ ቁጥር ያላቸው ትክል ድንጋዮች ይገኛሉ፡፡
የሰሙ አዋሾ ሰው ሰራሽ ዋሻዎች
በልዩ ወረዳው ከሚገኙ ሰው ሰራሽ ዋሻዎች መካከል አብዛኛዎቹ ዋሻዎች የሚገኙት ከሳጃ በ43 ኪሎ ሜትር ርቀት  በሚገኘው ሰሙ አዋሾ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ ዋሻዎቹንአጎራባች ገዥዎች ግዛታቸውን እና ሀይማኖታቸውን ለማስፋፋት በሚያነሱት ግጭት ጠላትን ለመከላከል፣ለማጥቃትና ራሳቸውን፣ ልጆቻቸውን እንዲሁም ንብረቶቻቸውን ለመሸሸግ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በወቅቱ ከ150-300 ዋሻዎች የተቆፈሩ ቢሆንም በናዳ፣ በጎርፍ እና በተለያዩ እንቅስቃሴዎች አሁን ላይ ቁጥራቸው ከበፊቱ ቀንሷል፡፡ ሁሉም ዋሻዎች የተለያየ መጠን አላቸው፡፡ መግቢያቸው እንዲሁም ውስጣቸው ጠባብና ሰፊ የሆኑ ዋሻዎችም ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ ዋሻዎች ባለ አንድ ክፍል ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ባለ ሁለት ክፍል ዋሻዎች ናቸው ፡፡   ባለ ሁለት ክፍል ዋሻዎችን ሰንመለከት አንዱ የከብቶች ማደሪያ ሌላው ደግሞ የሰውና የቁሳቁስ ማስቀመጫ በመሆን ያገለግሉ ነበር፡፡ በዋሻዎቹ ውስጥ የመኝታ፣ መደብ ለመቀመጫነትና ግርግዳው ተቦርብሮ ለዕቃ መደርደሪያነት መዘጋጀቱ እጅግ ድንቅ የሚያስብል እና ግርምትን የሚፈጥር ነው፡፡  


የቦር ተራራ  እና ባህላዊ የመድኃኒት ለቀማ /ጥቅምት 17/

ቦር ተራራ

የቦር ተራራ ከልዩ ወረዳው ዋና ከተማ ሳጃ በ32 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲገኝአራት ቀበሌዎችን ማለትም ሾሸርና አልማማ፣ሰሙ አዋሾ፣ላይኛውከሸሉን እና ሸሞና መተሎን ያዋስናል፡፡ከባህር ወለል በላይ 2939 ሜትር  ከፍታ  ያለው ቦር ተራራበልዩ ወረዳውከሚገኙ ተራሮች ትልቁነው፡፡ የተራራው አናት በአራቱም አቅጣጫ ያሉ አጎራባች ዞኖችን ማለትም የጉራጌሀዲያንናየከንባታ ጠንባሮ ዞኖችንእንዲሁምየጂማ ዞንን በርካታ ስፍራዎች በተጨማሪም ግልገልግቤ ቁጥር 1 ሀድሮ  ኤሌክትሪክይል ማመንጫ ግድብን እና ሌሎች ስፍራዎችን እንደልብ ያሳያል፡፡
የብሔረሰቡ አባላት በአንድነት ወጥተው ከተለያዩ እፅዋትመድኃኒት የሚለቅሙበት ዓመታዊ የመድኃኒት ለቀማ የሚከናወነው በዚሁ የቦር ተራራ ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ይህ ዓመታዊ መድኃኒት ለቀማ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ይከናወናል፡፡አብዛኛው ማህበረሰብ ለመድኃኒት የሚጠቀምበትን እፅዋት የሚለቅመው በዚህ ተራራ ላይ ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበውም የመጀመሪያው የማለዳ ፀሐይ የሚያገኘው በዚህ ስፍራ ላይ በመሆኑ በተራራው ላይ የሚገኙት መድኃኒቶች የመፈወስ አቅማቸው ከፍተኛ ነው ተብሎ ስለሚታመንበት ነው፡፡ በዓመቱ ተለቅሞ የሚቀመመው መድኃኒት በአካባቢው አጠራር ”ሳሞ ኤታ” ይባላል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠላቸውን፣ ስሮቻቸውን እና ቅርፊታቸውን በመሰብሰብ ቤታቸው ወስደው በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት የሚሆን መድሃኒትነት ይቀምሙበታል፡፡

No comments:

Post a Comment