Friday, October 2, 2015



ሳውላ ጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል እያስተናገደች ነው፡፡


የደምባ ጎፋ ወረዳና የሳውላ ከተማ አስተዳደር በጋራ የሚያዘጋጁትና የጎፋ ብሔረሰብን የመስቀል በዓል አከባበር ምክንያት አድርጎ የተዘጋጀው የጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ 


በመስቀል በዓል አከባበር ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም፣ የባህል ትዕይንት ዝግጅትና አውደ ርዕዮች የተካተቱበት የጎፋ ማስቃላ ፌስቲቫል በሳውላ ከተማ መስከረም 10 ቀን ተጀምሯል፡፡ በዓሉ መስከረም 11 ቀን በድምቀት ሲከበር የብሔረሰቡ የመስቀል ጭፈራዎች፣ ባህላዊ ትዕይንቶችና ደማቁ የደመራ በዓል በሳውላ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ በዝግጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች የታደሙ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የሳውላ ከተማና የደምባ ጎፋ ወረዳ ነዋሪዎች አድምቀውታል፡፡

No comments:

Post a Comment