Friday, October 2, 2015



አዲግራት የመስቀል በዓልን በድምቀት እያከበረች ነው፡፡



በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የምትገኘው የአዲግራት ከተማ የመስቀል በዓልን በድምቀት አከበረች፡፡ የመስቀልን በዓል ወደ ሀገራቸው ገብተው በማክበር የሚታወቁት ዓጋመዎች ዘንድሮም ለመስቀል አዲግራት ከትመዋል፡፡ በተለየ መልኩ ዝግጅት ያደረገችው አዲግራት በዓሉን በድምቀት አክብራዋለች፡፡


በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ያዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ የዝግጅቱ አንዱ አካል ነበር፡፡ ጉባኤው በምስረቃዊ ዞን የተደረጉ ምርምሮችና አርኪዎሎጂካል ጥናቶች ላይ የመነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ 




ዝግጅቱ በጎዳና ላይ ባህላዊ ትዕይንቶች የደመቀ ሲሆን የምሽት ችቦ ማብራት ስርዓቱና የደመራ ስነ ስርዓቱ እጅግ ደማቅና ከወትሮው የተለየ ሲሆን በደመራ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በርካታ የስራ ሃላፊዎች ታድመውበታል፡፡

No comments:

Post a Comment