Saturday, October 10, 2015

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተሟላ ጥንተ-አፍሪካዊ ዘረ-መል/GENOME/ ተገኘ


በሀገራችን ደብቡ ክልል ጋሞ በተባለ መካነ-ቅርስ ከፍተኛ ስፍራ ሞጣ በሚባል ዋሻ እድሜው 4 500 ዓመት የሚገመትባይራየተሰኘ የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል ተገኘ፡፡
ከግኝቱ ላይ በጥንቃቄ በተወሰደ ናሙና በእፍሪካ በዕድሜ ከፍተኛ የሆነውን የዕድሜ ዘረ-መል አወቃቀር ማወቅ ተችሏል። የግኝቱን ስያሜ በተመለከት የጥናት ቡድኑ የተገኘበትን የጋሞ ማህበረሰብ ቋንቋ መሰረት ባደረገ ሁኔታ "ባይራ" ብሎ የሰየመው ሲሆን ትርጉሙም የበኩር ልጅ እንደማለት ነው።
እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 2011 በካትሪን አርተር የሚመራው ዘርፈ ብዙ የጥናትና ምርምር ቡድን በጋሞ ማህበረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች መሪነት የሞጣ ዋሻን የጎበኘ ሲሆን በወቅቱም በሰበሰቧቸው መረጃዎች መሰረት ሌሎች ባለሙያዎችን በማካተት 2012 በከፊል ባደረገው ቁፋሮ "ባይራ" የተባለውን ቅሪተ አካል ማግኘት ችሏል።
"ባይራ" 30 እስከ 50 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ኖሮ የሞተ የአዋቂ ወንድ ቅሬተ አካል እንደሆነ በጥናቱ መረጋገጡን የቅርስ ጥናንትና ጥበቃ ባለስልጣን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህ ግኝት ከቅሪተ አካሉ በተጨማሪ በመቃብር ጉድጓዱ ውስጥ በርከት ያሉ ከባልጩት ከጥቁር ድንጋይ እና ከሌሎችም የድንጋይ አይነቶች የተሰሩ ፍላጭ የድንጋይ መሳሪያዎች የተገኙ ሲሆን እነዚህም የሚያመላክቱት የኋለኛው የድንጋይ ዘመን የድንጋይ መሣሪዎች ስብስብ መሆናቸውን ነው፡፡
ቅሪተ አካሉ የመጀመሪያውን ጥንታዊ ዘረ-መል ቅንጅታዊ ስርዓትን በአፍሪካ ከማሳየትም በላይ የሰው ዘር ፍልሰት ከዩሬዥያ ወደ አፍሪካ ቀንድ ቀድሞ ከሚታወቅበት ጊዜ 3000 ዓመት ወደ ኋላ እንዲገፋ አድርጓል፡፡ እድሜ ጠገቡ ቅሪተ አካል ስለ ጥንታዊው የሰው ዘር በርከት ያሉ መረጃዎችን ለማፈላለግ ይረዳል እየተባለ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment