Monday, August 31, 2015

አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፣ ባዛርና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው፡፡




የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሬክቶሬት፣የፋሽንና ዲዛይነሮች ማህበራትና ሜኖናይት ኢኮኖሚክ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን / MEDA/ በመተባበር የኢትዮጵያ ፋሽን አዲስ  ገልፅታ /New Images of Ethiopian Sustainable Fashion/ በሚል መሪ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የባህል ልብስ አምራቾች ፤ ዲዛይነሮች ሌሎች መሰል አካላት ባሳተፈ መልኩ አገር አቀፍ የፋሽን ትርት፤ ባዛርና አውደ ርዕይ ከነሐሴ 26 እስከ ነሐሴ 30 2007 ዓ.ም በኦሮሞ የባህል ማዕከል ይከናወናል፡፡


ዘርፉ ያለው እምቅ ኢኮኖሚያዊ አቅም ለሃገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ማስተዋወቅ፣ በዘርፉ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ የዘርፉን ቀጣይ እድገትና ከዘርፍ የሚጠበቀውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲበራከት ማስቻል፣ በዲዛይንና ፋሽን ጥበብ ውስጥ ያሉ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች እርስ በእርሳቸው ልምድና ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ማስቻል፣ የህፃናት የጉልበት ብዝበዛን በማስቀረት ጤናማ የእሴት ሰንሰለት የመፍጠር እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ማሳየት እና ሌሎች ዓላማዎችን ይዞ የተነሳ ዝግጅት ነው፡፡
በ5 ተከታታይ ቀናት ቆይታው የኢትዮጵያ ዲዛይንና ፋሸን ጥበብ እድገትና ተግዳሮቶች በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት ይደረጋል፣ ከ6 ክልሎች የሚመጡ የባህል ልብስ አምራቾች ሸማኔዎች ስራዎቻቸውን ምርቶቻቸውን ለእይታና ለሽያጭ ያቀረባሉ፣ ከፋሽን ዲዛይነሮች ማህበር በሚሳተፉና ተጋባዥ ዲዛይነሮች የአልባሳት ሽያጭ ዓውደ ርዕይ ፣ የፋሽን ትርዒት እንዲሁም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዘጋጀውና ለብዝሃን ህብረተሰብ ተደራሽ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ዝግጅት 150 በላይ ተሳታፊዎች (ኢግዝቢሽን አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ሲሆን የዲዛይነር ትምህርት ቤቶችም ተካተዋል፡፡ ነሀሴ 26/2007 ዓ. ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን መግቢያው በነፃ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment