Tuesday, February 23, 2016


በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰቆጣ ከተማ ተከበረ፡፡
 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ የሆነው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በኢትዮጵያም በየዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከበር ቆይቷል፡፡ የዘንድሮው በዓል በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከአዲስ አበባ በ720 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰቆጣ ከተማ ከየካቲት 13-15/2008 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡

እንደፈረንጆቹ ቀን ቀመር በ1952 ዓ.ም. ፌብሪዋሪ 21 ቀን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን ሆኖ እዲከበር በተወሰነው ውሳኔ መሰረት በዓሉን የምታከብረው የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ 46 የሚደርሱ ቋንቋዎች በአፍ መፍቻ ትምህርት እንዲሰጥባቸው ያስቻለች ሀገር ናት፡፡

ከተለያዩ ክልሎች ከከፍተኛ የመንግስት ተቋማትና ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበትን ይህንን ጉባኤ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዳይሮክተሬት ክፍል ትምህርት ሚኒስቴርና ኤስ አይ ኤል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን የተለያዩ የጥናት መነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ክልሎች በቋንቋ ልማት ያከናወኗቸውን ሪፖርቶች አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

 

No comments:

Post a Comment