Wednesday, February 17, 2016

አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ደረሱ፡፡
አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ሲደርሱ የገዳ አካላት ከጉሚ እየወጡ ነበር፡፡ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ከኦሮሞ ባህል ማዕከል በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት የተንቀሳቀሱት ስምንት ሴቶችና አስራ አምስት ወንድ ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ 32 ልኡካንን ይዘዉ እንደመጡ የገለጹት የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ግዛዉ ተወዳዳሪዎቹ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ተመልምለው የመጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የብስክሌት ተወዳዳሪዎቹ በአለፉባቸው ጎዳናዎች የአባ ገዳን ሥርዓት ለማስተዋወቅና በዚህ ስፖርት ተነቃቅተዉ ተተኪን የማፍራት ዓላማን እንዳነገቡ አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ውድድሩ ሁለት ዓይነት ሲሆን የጎዳናና የዙር ዉድድርን ያካተተ ነው፡፡ ይህ ትናንት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ዛሬ መኤ ቦኮ የደረሱበት ውድድር የጎዳና ዉድድሩ አካል ሲሆን ይህም በስኬት ተጠናቋል፡፡ የዙር ዉድድሩ የጉጂ ዞን መቀመጫ በሆነችዉ የነጌሌ ከተማ በነገዉ እለት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment