Friday, March 4, 2016


ዓለም አቀፉ የዱር እንስሳት ቀን በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀምሯል፡፡

ፎቶ፡- የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ /ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ/

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 68ተኛ ጠቅላላ ጉባዬ የዱር እንስሳት ቀን በየዓመቱ ማርች 3/ የካቲት24/ እንዲከበር ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የዘንድሮ የዱር እንስሳት ቀጣይ ህልውና በእጃችን ነው !!  በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ 3ተኛ ጊዜ በአገራችን 2 ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡


የመጀመሪያው የዱር እንሰሳት ቀን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ በጭሮ ከተማ የተከበረ ሲሆን የዘንድሮ ከየካቲት 24 ጀምሮ ለአንድ ወር በተለያዩ ፕሮግራሞች ቆይታውን አድርጎ ከመጋቢት 24-26 በባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በሚከናወን ዝግጅት ይጠቃለላል፡፡ በቆይታውም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት፣ ጉብኝት፣ጥያቄና መልስ፣ በዘርፉ አስተዋፅኦ ላደረጉ ጀግኖች እውቅና መስጠት፣ ግንዛቤን የመፍጠር ስራዎችና ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወኑ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልፃዋል፡፡

የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳውድ ሙሜ የዱር እንስሳት ቀን በየአመቱ ሲከበር የዱር እንስሳት ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን የመቀነስ ዓላማን ይዞ መሆኑንና በተለያዩ ፕሮግራሞች መከበሩ ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሳካት ግንዛቤና ንቅናቄ የሚፈጠርበት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 2017 .. ኢትዮጵያን በዘላቂ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ አጠቃቀም ከመጀመሪያዎች 5 የአፍሪካ አገራት አንዷ የማድረግ ራዕይ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ስር ከሚተዳደሩት 13 የጥበቃ ቦታዎች በዓመት 6.5 ቢሊየን ብር ገቢ ተደርጓል፡፡

No comments:

Post a Comment