Wednesday, August 3, 2016


        የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሮክተሬት በ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም ተሸላሚ ሆነ፡፡

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በዘርፍ ከሚገኙ የፌዴራል የኮሙኒኬሽን አደረጃጀቶች መካከል የ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላመጡ እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በላቀ አፈጻጸም የሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ለመሸለም በቅቷል፡፡ ሽልማቱ ተመሳሳይ የሆኑ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን እና የፌዴራል ተቋማትን የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሮክተሬቶችን ያቀፈ የአፈጻጸም ውድድር ተደርጎ የተገኘ ውጤት መሆኑም ታውቋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛህኝ አባተ የፌዴራል ተቋማት የኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ዓመታዊ የጋራ ፎረም ላይ በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

 

No comments:

Post a Comment