Friday, April 24, 2015

2ኛው ሀገር አቀፍ የግእዝ ጉባኤ

በሀገራችን ከሚገኙ ጥንታዊ ቋንቋዎች አንዱ ግእዝ ነው፡፡ በርካታ ታሪኮች በዚሁ ቋንቋ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ በግእዝ የተጻፉ መዛግብትን መርምሮ ለመጠቀም ቋንቋውን ማወቅና መጠቀም የግድ ቢልም የግእዝ ቋንቋ ተናጋሪዎችም ሆኑ አንባቢዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የሚገኙ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ግእዝን ከብዙሃኑ ህዝብ አራራቀው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ ለግእዝ ባይተዋር የሆነ በሚሊዮን የሚቆጠር አዲስ ትውልድ ተፈጠረ፡፡ ቋንቋው ከቋንቋነት ባለፈ በያዛቸው ፋይዳ ያላቸው እውቀቶች፣ ሀገራዊ እሴት በመሆኑና ብቸኛው የአፍሪካ የራሱ ፊደል ያለው ቋንቋ በመሆኑ ሊጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሊለማም ይገባዋል፡፡ ሁለተኛው የግእዝ ጉባኤም ይህንኑ ዓላማ መሰረት አድርጎ ከመጋቢት 22 እስከ 23 ቀን 2007 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

አምና በተመሳሳይ መልኩ አክሱም ካስተናገደችው የመጀመሪያው ጉባኤ አንድ ደረጃ ከፍ ብሏል የተባለለት የዘንድሮው የግእዝ ጉባኤ የመስክ ጉብኝቶችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ ይህ ጉባኤ በርካታ ምሁራን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራማሪዎች፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ጨምሮ ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት ታድመውበታል፡፡ ዝግጅቱን ያዘጋጀው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዳይሮክተሬት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማእከልና ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ጋር በመተባበር ነው፡፡
ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው ስምንት የሚደርሱ የውይይት መነሻ የጥናት ጽሑፎች ቀርበውበታል፡፡ እነዚህም በቅድመ ክርስትና ተቀርጸው የተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ለኢትዮጵያና ለአካባቢው ያላቸው ታሪካዊ ፋይዳ በሚል በዶክተር ስርግው ገላው፣ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የሚለው የውይይት መነሻ ጽሑፍ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣
 የግዕዝ ሥነ-ጽሑፍ ጥቅም ለመካከለኛው ኢትዮጵያ ጥናት በዶክተር መርሻ አለህኝ፣ ባህረ ሀሳብና ግዕዝ በጋዜጠኛና የባህረ ሀሳብ ተመራማሪ ሄኖክ ያሬድ፣ የግዕዝ ቅኔና ፍልስፍናው በዶክተር ሙሉቀን አንዱዓለም፣
የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በአራቱ አድባራት ወ ገዳማት በሊቀ ህሩያን ተግባሩ አዳነ በመጀመሪያው ቀን የቀረቡ ሲሆን ዶክተር አምሳሉ ተፈራ፣ ዶክተር ሀይሉ ሀብቱና መምህር ደሴ ቀለብ ውይይቶቹን መርተውታል፡፡
ሁለተኛው ቀን በዶክተር አባ ዳንኤል ግዕዝና ሥነ-ጽሑፍ በሚል ርዕስ ዙሪያ በቀረበው መነሻ ውይይት ተደርጓል፡፡ የማጠቃለያው ውይይት በዶክተር እልፍነሽ ሀይሌ የተመራ ሲሆን በጉባኤው የታደሙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉጌታ ሰይድ ቋንቋውን ለማልማት ሁሉም ሰው የየራሱን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ገልጸዋል፡፡
ዝግጅቱ ታሪካዊ የሆኑትንና በቅኔና አብነት ትምህርት ተቋምነታቸው የሚታወቁትን የምስራቅ ጎጃም ጥንታዊ አድባራትን የመጎብኘት መርሀ ግብርን አካቷል፡፡ በዚህም ደብረ መዊዕ፣ ደንበጫ ሚካኤል፣ ደብረ ኤልያስ፣ ዲማ ጊዮርጊስና ደብረ ወርቅ ማርያምና የአብነት ትምህርት ተቋሞቻቸው ተጎብኝተዋል፡፡ 

ቀጣዩ የግእዝ ጉባኤ ሳልሳይ መሆን ብቻ ሳይሆን ከነበረው አንድ ደረጃ ከፍ ያለ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ይህ መሆን ከቻለ ተከታታይነት ባለው መልኩ ጉባኤውን የማሳደግ ሂደቱ ስኬታማ መሆን ይችላል፡፡ ከእምነት ጋር ተጣብቀው የሚታዩት የግእዝና የአረብኛ ቋንቋዎች በሀገራችን ፋይዳ ያላቸው ቋንቋዎች ሆነው ሳለ ትኩረትን ተነፍገዋል፡፡ በቀጣይም እንደ ግእዙ ጉባኤ ሁሉ የአረብኛና ሌሎች ጥንታዊ ቋንቋዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ እንታደም ይሆናል፡፡
የግእዝ ጉባኤው ተጀምሯል፤ ሁለት ዓመታትንም በስኬት ተካሂዷል፡፡ አቶ አለማየሁ የቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዳይሮክተሬት ባለሙያ ናቸው፡፡ ቀጣዩ ጉባኤ ግእዝን ከሁሉም የሀገራችን ቀጠና ጋር ማስተሳሰር እንደሚቻል ይገልጻል፡፡ ግእዝን ከጋሞ ጎፋዋ ብርብር ማርያም፣ ግእዝን ከጉራጌ ዞኑ ምሁር ኢየሱስ ገዳም፣ ግእዝን ከምዕራብ ሀረርጌው ደብረ አሰቦት ገዳም፣ ግእዝን ከምስራቅ ሸዋው ዝቋላ ገዳም፣ ግእዝን ከደብረ ሊቦኖስ፣ ግእዝን ከዘርያቆብና ከደብረ ብርሃን ጋር ግእዝ አቅጣጫ ሳይወስነው ሁሉም የሀገራችን ቀጠና ልንወያይበት፣ ልንመክርበትና ልናለማው ይገባናል፡፡ ሶስተኛው ጉባኤና ቀጣዮቹ ጊዜያት ግእዝን የመታደግ ብቻ ሳይሆኑ ከግእዝ የምንፈልገውን የምናገኝበት እንዲሆኑ መረባረብ ይገባናል፡፡

No comments:

Post a Comment