Monday, December 12, 2016



የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚደግፉ ልምዶችን ለመቅሰም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በኬኒያ እየተደረገ ነው፡፡




በሀገራችን ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች አንዱ የሆነውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጣይ ስራዎች ሊደግፍ የሚችል የልምድ ልውውጥ በኬኒያ እየተደረገ ነው፡፡ በዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አዘጋጅነት በፍራንክፈርት ዙኦሎጂካል ሶሳይቲ የባሌ ተራሮች ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ እና በአጋር አካላት ትብብር ጥምረት የተዘጋጀው ይህ የልምድ ልውውጥ በኬኒያ የስምንት ቀናት ቆይታ ይኖረዋል፡፡
የኬኒያ የልምድ ልውውጥ ጉብኝቱ ከፓርላማ፣ ከኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣ ከኦህዴድ ጽ/ቤት፣ ከባሌ ዞን አስተዳደር፣ ከባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እና ከዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የተውጣጡ አስራ አምስት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን እየተካፈሉ ሲሆን በኬኒያ የሚከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ የዱር እንስሳት አያያዝና ልማት፣ የሰው ሃይል አጠቃቀም፣ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች አተገባበር እና የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ስልቶችን ተዘዋውሮ ይጎበኛል፡፡ አቻው በሆነው የኬኒያ ዱር እንስሳት አገልግሎት የስራ ሃላፊዎችም ሰፊ ገለጻ የተደረገለት ሲሆን በጉብኝቱ የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ብዝሃ ህይወት አስተማማኝ በሆነ አግባብ ለመጠበቅ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን፣ የማኔጅመንት ፕላን፣ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተጀመረውን እንቅስቃሴና እና የልማታዊ ባለ ሀብቶችን ሚና የተመለከቱ ልምዶች የተገኙበት ጉብኝት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment