Saturday, June 13, 2015



           6ተኛው የአዲስ አበባ የባህል ሳምንት ተጀመረ፤
ሜሮን ታምሩ
ከሰኔ 5 እስከ 7 2007 ዓ.ም. በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ሳምንት ልማታዊ ባህሎቻችን ለህዳሴ ጉዟችን ስኬት! የሚል መሪ ቃል አንግቧል፡፡ የባህል ሳምንቱ በባህሉ የሚኮራ፣ በማንነቱ የሚመካ፣ ትውልድ በመፍጠር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና መጤ የሆኑ ጠቃሚነት የሌላቸው ባህሎች መከላከልና ወደ ልማት የሚመጣ ህብረተሰብ መፍጠር፣ የኪነ-ጥበብ ዘርፉ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ማራመድ መቻል እንዲሁም ባህሎቻችንን ከማሳደግ ጎን ለጎን አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ እንደመሆኗ እንዲሁም አዲስ አበባ የአገራችን ርዕሰ መዲና ከመሆኗ ጋር በተያያዘ በርካታ ባህሎች ከተማችን ላይ ይንፀባርቃሉ ያለባበስ፣ የአጋጊያጥ የአመጋገብ ስርዓቱ እርስ በእርስ በማገናኘትና በማዋሀድ የተሻለ ባህል እንዲኖር ያግዛል፡፡

በባህል ሳምንቱ ላይ ክፍለ ከተማዎች፣ የባህል ልብስ የሚያመርቱ፣ የሚሸጡ፣ ባህላዊ ጌጣጌጥ የሚያዘጋጁ፣የቆዳ ውጤቶች፣ ባህላዊ መጠጦችን የሚያዘጋጁ፣ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች የሚያቀርቡ፣ ቲያትር ቤቶች፣ ቤተ-መፅሐፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ሌሎችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
አውደ ርዕዩ በሶስት ቀናት ቆይታው በሚከናወነው ሲምፓዚየም ላይ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ በተለይ በህፃናትና ሴቶች ላይ እያደረሰ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ምን ይመስላል? በሚለው ርዕሰ ጉዳይና የህብረተሰባችን የማንበብ ባህል ለማዳበር የሚያነብና ችግር የሚፈታ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችል ጥናዊ ፅሁፍ ይቀርባል፡፡
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ወርቁ መንገሻ አውደ ርዕዩ በጎ የሆነ የውድድር መንፈስ የሚፈጠርበት፣ ሀገር በቀል ምርቶችን በማሳደግ የገበያ ትስስር መፍጠር፣የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ባህላችንን የሚጎዱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በመከላከል ወደ ምዕራብያኑ ከመሳብ ይልቅ የአገራችንን ምርቶች እያሻሻልን ተቀባይነት እንዲኖራቸው በማድረግ አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ባህል ባለቤት እንደመሆኗ የኛ ባህል የራሳችን ማንነት ነውና አውቀን ልናሰፋው ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ከዛ በኋላ ሌሎች ወደኛ ይመጣሉ እንጂ እኛ ወደነሱ የምንሄድበት ነገር አይኖርም ሙሉ የሆነ ባህል አለን እዚህ ላይ በደንብ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment