Saturday, September 22, 2012


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች በባህር ዳር ከተማ ከትመው የዓመቱን አፈጻጸም ገመገሙ!

ጎንደር 1ኛ ደረጃነቷን  አስጠብቃለች፡፡

ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡


ከመስከረም 7 ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም ባህርዳር የተሰበሰቡት የባህልና ቱሪዝም ሴክተር ተቋማት በዋናነት ዓመታዊውን አፈጻጸማቸውን የገመገሙ ሲሆን መርሀ-ግብሩ በክልሉ ባህል፣ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ የተዘጋጀ ነው፡፡

በአፈጻጸም ደረጃ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ቀጥሎ የቱሪዝም ዳይሮክተሪዋን ባስመረቀች ማግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በተያዘው ዓመት አያሌ የተለዮ ተግባራትን ያከናወነችው ጎንደር ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የሙዚየም ቀን ተከብሮባታል፡፡ ከአማርኛ ቋንቋ ባሻገር በትግራይ በነበረው የከተሞች ቀን ላይ በትግርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ የፕሮሞሽናል ቁሳቁሶች እራሷን ያስተዋወቀችው ጎንደር፤ በዚሁ ዓመት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ባለድርሻዎችን ያካተተ የቱሪዝም ገቢ አመንጪ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ የገባችበት ዓመት ነበር፡፡




በሥነ-ሥዕል፣ በኪነ-ጥበብ እና መሰል የባህል ዘርፎች አያሌ ክንውን አድርጋ ያሳለፈችበት ይህ ዓመት የተሳካ ብሔራዊ የባህል ትእይንት በማካሄድ የሚዲያ ትኩረትን ስባ የከረመችበት ዓመት ነበር፡፡

በመስከረም 6 ቀን 2005 ዓ.ም በቋራ ሆቴል የተመረቀው የጎንደር ቱሪዝም ዳይሮክተሪ ከተማዋን የመስህብ ሃብቶች የሚያስተዋውቅ  ሲሆን የተዘጋጀውም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡ ይህ በሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽንና በከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ትብብር የተዘጋጀው ዳይሮክተሪ በቀጣይ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይቀርባል፡፡

በአፈጻጸም ደረጃ በ2004 ዓ.ም የብዙዎችን ትኩረት የሳበ የባህል ፌስቲቫል አዘጋጅቶ የነበረው የምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለተኛ ደረጃ ሲይዝ፣ የባህል ማእከል እየሆነ የመጣውና በፈረስ ትርኢት ዝግጅት የተዋጣለት ስራ የሰራው አዊ ዞን ሶስተኛ ሆኗል፡፡

      

No comments:

Post a Comment