Friday, May 20, 2016

ዓለም አቀፉ የሙዚየም ቀን ተከበረ



 የዘንድሮ የዓለም የሙዚየም ቀን‹‹ ሙዚየሞችና ባህላዊ መልክዓ ምድር!››/ Museums and Cultural Landscape/ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ጊዜ በአገራችን 14 ጊዜ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተከበረ፡፡
በተፈጥሮአዊና ባህላዊ የመልክዓ ምድር አያያዝና አጠቃቀም ፣ በጥምር ደንና የግብርና ሥርዓት  በዓለም ቅርስነት ባስመዘገበው በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መከበሩ ልዩ ያደርገዋል፡፡  በክልሉ ከተማዎች ማለትም  በሐዋሳ ፣ በአርባ ምንጭ ፣ ቱርሚ፣ በጅንካና በኮንሶ አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ከግንቦት 06   እስከ ግንቦት 12  2008 . የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውነዋል፡፡


የሙዚየም ቀንን ለማክበር በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ሙዚየሞች የተገኙ ተወካዮች፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሰራተኞች የሚዲያ አካላት እንዲሁም ከተለያዩ ተጠሪ ተቋማት የተገኙ እንግዶች ቅዳሜ ግንቦት 6 ቀን መነሻቸውን አዲስ አበባ አድርገው  ሀዋሳ ሲደርሱ በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በማግስቱም ልኡካኑ ወደ  አርባምንጭ ያቀኑ ሲሆን  አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱም የከተማው ነዋሪዎች  በባህላዊ ሙዚቃ በመታጀብ በደማቅ ሁናቴ እንኳን ደህና መጣቹ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡  በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ግንቦት 8 በተካሄደው ሲምፖዚየም ላይ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዩናስ ደስታ፣ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ፕሬዘዳንት / ዳምጠው ዳርዛ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የሙዚየም ባለሙያዎች ፣ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ምሁራን  እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡  ሙዚየሞችን የማስፋፋት አስፈላጊነት፣ የሙዚየም ታሪክ ዓለማቀፋዊና አገራዊ አንድምታ፣ በደቡብ ክልል /// ውስጥ የሚገኙ ሙዚየሞች ላይ ያሉ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ምሁራን ጥናት አቅርበው ከታዳሚው ጋር ውይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡ በቀጣይ ቀንም አከባበሩ በተለያዩ ስርዓቶች የቀጠለ ሲሆን የሉካን ቡድኑ ወደ ቱርሚ በመጓዝ የባህላዊ ከብት ዝላይ እንዲሁም የኢቫንጋዲ ጭፈራ ስነ-ስርዓት ታድመዋል፡፡ ቀኑ ታስቦ በሚውልበት ግንቦት 10 ቀን 2008 .. / May 18 2016 / ቡድኑ በጅንካ ከተማ በመገኘት የተለያዩ ፕሮግራሞችን አከናውኗል፡፡  ስለ ‹‹Open Air Museum›› ምንነትና አስፈላጊነት፣ ባህላዊ መልክዓ-ምድር ምንነትና ባህላዊ እሳቤ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጥያቄና መልስ ወድድር እና የምስጋና የሽልማት ስነ-ስርዓት ተከናውነዋል ፡፡ ግንቦት 11 ልኡካን ቡድኑ ወደ ኮንሶ ጎራ በማለት የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ጎብኝቶ ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ አድርጓል፡፡






No comments:

Post a Comment