Monday, December 2, 2013




የብዝኃናነት ስብጥርና የቀለሙ ፋይዳ

Harer
ወጥ ከሆነ ቀለም ህብራዊነት ውበት አለው፡፡ አበቦች ከእጽዋት በበለጠ ሳቢና የመንፈስ እርካታ ምክንያት የሆኑበት ሚስጥር ህብረ ቀለማዊነታቸው ነው፡፡ እንደማንኛውም የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች ሁሉ ክቡሩን የሰው ልጅም ህብራዊ ስብጥሩ ያደምቀዋል፡፡ ለሰው ልጅ ህብራዊነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ የሰው ልጅ ህብራዊነት ከአያሌ ነገሮች ይቀዳል፡፡ ቋንቋው፣ ኃይማኖቱ፣ ባህሉ፣ መልከዓ ምድራዊ መኖሪያው እና የአካባቢው ተጽእኖ እና ሌሎች እልፍ መነሾዎች አሉት፡፡

ለሰው ልጅ ልዩነቱ እንደየተቧደነበት ምክንያት ተፈጥሮአዊ ስጦታው ነው፡፡ መልኩ ብዙነቱን ጠብቆ ለማኖር ግን ቀዳሚው ነገር ያንን ህብራዊነት እንደ አበባ ተፈጥሮአዊ ውበት ሊረዳው፣ ሊያጌጥበትና ሊጠብቀው ሲገባ ነው፡፡ ዩኔስኮ የመቻቻል ቀን በሚል ኮንቬንሽኑን የፈረሙ ሀገራት እንዲያከብሩት የሚያደርገው በዓል ዋንኛ ምክንያቱ እንደ ተፈጥሮ ሁሉ የሰው ልጅም ብዝኃነት በዓለም ወደ አንድ መንደርነት መቀየር ሳቢያ እልፍ የነበረው የሰው ልጅ ብዝኃነት ወጥና አንድ ሆኖ እንዳይጠፋ የሚያስችል አጀንዳ ያለው ነው፡፡

ሀረር ይህንን በዓል በኢትዮጵያ ደረጃ በወርሐ ህዳር አስተናግዳዋለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ ህዳር 7 የሚከበረው የመቻቻል ቀን ላለፉት ሶስት ዓመታት በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀረር ከተማ ላይ ተከብሯል፡፡ ከበዓሉ አስቀድመው ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ሙሉጌታ ሰይድ በዓሉ የባህል ቱሪዝም ምርትን ለምትሸጠው ኢትዮጵያ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርት በመሆን ጭምር የሚያገለግል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮው በዓል ከጎዳና ላይ ኩነትነት ባሻገር ለውይይት መነሻ የሆኑ የጥናት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ሀረር በእግርጥም በብዙ መልኩ ህብራዊነትን ትወክላለች፡፡ በዓለም ላይ የተለየ ሊባል የሚችል አፍሪካዊ የሆነ ኢስላማዊ ባህል የሚንጸባረቅባት የስልጣኔ መገለጫ ናት፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ብዙና የተሰባጠረ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ መሆኗ የበለጠ እንድትወደድና ለስኬት ቅርብ እንድትሆን አድርጓታል የሚል እምነት አላቸው፡፡ ቀላልና ተግባቢ ከተሜዎች የሚኖሩባት ይህች የዓለም ቅርስ የታሪክና የቅርስ ብቻ ሳይሆን የባህል ቱሪዝምም አውድ ናት፡፡ በዓይነታቸው ወጣ ያሉ እንደ እንስሳት ቱሪዝም መሰል የቱሪስት መዳረሻዎችንም ይዛለች፡፡
ከሀኪም ጋር ስር በተዘረጋችው ሀረር የተከበረው የመቻቻል ቀን ሀረር ብቻ ሳትሆን ድፍን ኢትዮጵያ የተቸረችው ብዝኃነት የማንነት መገለጫ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አዕማድም ነው፡፡ የመቻቻል ጠቀሜታም ይህ ህብርነት በየትኛውም ተጽእኖ እንዳይጠፋ ህዝቦችም ይህ እንዲከሰት የሚያደርግ ኩነትን ሁሉ በመቻቻል መንፈስ አልፈው ከቀደሙት አባቶቻችን የወረስንውን ብዝኃነት ካለው እልፍ ፋይዳ አኳያ ልንጠብቀው ይገባል፡፡ ልዩነት ለጠነከረ አንድነት መሰረት እንጂ ስጋት አይደለምና በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ ስብስብ ውበትም እውነትም ነው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ ገንዘብም….
 
 

No comments:

Post a Comment