Saturday, April 14, 2012


ዜና
ዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2004 ዓ.ም

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሪት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ…. የመጨረሻ ቀን

ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን ከየኔታ መኖሪያ ቤት/አልፋ ቪላ/ እስከ ዞር ኃይሎች በእግር በመጓዝ ሸኝተዋል፤

ስራቸው ህያው በመሆኑ ቀብር ሳይሆን ሽኝት ነበር፤

በሽኝቱ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣አምባሳደሮች፣የሙያ ልጆቻቸውና አድናቂዎቻቸው ተገኝተዋል፡፡


እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሪት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ…. በሚወዳቸው፣በሚያከብራቸውና ዘመናቸውን ስለ ክብሩ በኖሩለት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘለዓለም ተሸኝተዋል፡፡ ለስምንት አስርት ዓመታት የኖሩባት ኢትዮጵያ የኖሩላትን ያክል ውለታቸውን ባትመልስም፣ አፍቅረዋታል….ፍቅራቸው ደግሞ የአፍ አልነበረም፣ ገልጸውታል…..ትውልድ የሚጋራውን ፍቅር…. ህይወት ዘርተውበታል፡፡



አንድ ወቅት በርካታ ጋዜጠኞች በታደሙበት አንድ ዝግጅት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሪት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ለማናገር ማን እንዴት አድርጎ ስማቸውን ይጥራ? በኃላ የሪፖርተሩ ሔኖክ ያሬድ የኔታ ሲል ጠራቸው፣ በርግጥም ይህንን ስም እጅግ አድርገው ወደውት ነበር…. እኛም የኔታ እያልን እንቀጥል…..


የኔታ ታሪካዊ በሆነችው ደጋማዋ አንኮበር 1925 ዓ.ም. ከእናታቸው ከእመት ፈለቀች የማታ ወርቅና ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ ተወለዱ፣ ከማህበረሰባቸው፣ከሃገራቸው መልክ፣ ከቀደሙት አባቶች፣ከሃገር እና ከዓለም አቀፍ እውቀትን ቀሰሙ….እውቀት ሆኑ….በእውቀታቸው ሃገራቸውን….አገለገሏት…. እንደሃገራቸው ነጻነት የእሳቸው እውቀት ለጥቁር ህዝቦች ደረሰ…. የአፍሪካውያን ጌጥ እና ኩራት ሆኑ…









  
ሚያዝያ ስድስት ቀን ለመጨረሻ ግዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ሲሸኙ… ሽኝቱን በጸሎት ሲመሩት የነበሩት ቅዱስ አባታችን አቡነ ጳውሎስ እንዲህ ሲሉ ለትውልድ ተናገሩ….."እኚህ ሰው የዓለምን አፍ ዘግተዋል….ለተቺዎች እድል አልሰጡም"

የረጅም ዓመት ወዳጃቸው ገጣሚ፣ ደራሲና ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላት መሳጭ፣በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን እና የኔታን በጨረፍታ የሚያስተዋውቀውን የህይወት ታሪክ ሲቃ እየተናነቀው አቅርቦታል….


እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሪት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በመጨረሻም የመጨረሻው ሽኝታቸው ተፈጽሟል፡፡

No comments:

Post a Comment