Monday, December 12, 2016



የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚደግፉ ልምዶችን ለመቅሰም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በኬኒያ እየተደረገ ነው፡፡



Monday, November 7, 2016



4ኛው የኢትዮጵያ ዋርደኖች ጉባኤ፤ 

አርባ ምንጭ ከተማ ከጥቅምት 24 እስከ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ዓመታዊውን የኢትዮጵያ ዋርደኖች ጉባኤ አስተናግዳለች፡፡ የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ወደብ ከተማ የሆነችው እና ከአዲስ አበባ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አርባ ምንጭ ያስተናገደችው የዘንድሮው ጉባኤ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነበር፡፡

Thursday, October 20, 2016



አዲሱ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ብራንድ እና ቀጣዩ የመገናኛ ብዙኃን ሚና

=====================================
ኢትዮጵያ የመለዮ ስያሜውን LAND OF ORIGINS ያደረገ አዲስ የቱሪዝም አርማ እና መለዮ ስያሜ ይፋ አድርጋለች፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጉት አዲሱ የመለዮ ስያሜ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያክል የአስራ ሦስት ወር ጸጋ በሚል ሲያገለግል የኖረውን ብራንድ ስያሜ የሚተካ ነው፡፡

Friday, October 14, 2016


የመስቀል በዓል አከባበር በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ
ጢያ ትክል ድንጋይ-ሶዶ ወረዳ
 

የመስቀል በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበት፣ የተነፋፈቁ ናፍቆታቸውን የሚወጡበት፣ ያለፈው ጊዜ ምን እንደሚመስል መጪው ጊዜ ምን መሆን እንዳለበት የሚወስኑበት ለክብረ በዓሉ በሰላም ላደረሳቸው ፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡበት ለወደፊቱም መልካም ምኞታቸውን የሚገልፁበት አጋጣሚ ነው፡፡ መስቀል የክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ማህበረሰባዊ ልማዱን ከትውልድ ትውልድ ከሚያስተላልፍባቸው ሀገራዊ ልማዶች መካከል አንዱ በዓል ነው፡፡

Saturday, September 10, 2016


ጎፋ ጋዜ ማስቃላ 2009 በዛላ ወረዳ ይከበራል፡፡
 

በጎፋ ብሔረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል ጎፋ ጋዜ ማስቃላ 2009 በዛላ ወረዳ በድምቀት ይከበራል፡፡ ከመስከረም 9-10 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚከበረው ይህ በዓል በጎፋ ብሔረሰብ የተለዩ እሴቶች የሚደምቅና ጊያ ካንሶ በሚባለው የመስቀል በዓል ሽኝት ሥነ-ሥርዓት የሚታጀብ ነው፡፡

Friday, August 26, 2016


አሸንዳ 2008 በዓል በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡
Photo; Ashenda festival in Mekelle

አሸንዳ 2008 ባህላዊ ኩነት በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው ይህ በዓል ከመቐለ ከተማ ውጪ በተንቤን አብይ አዲም በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ችለናል፡፡


ሻደይ 2008 ፌስቲቫል በድምቀት ተከበረ፡፡
Photo: shaday festival 2016 wagehimera zone
ሻደይ 2008 የባህል ፌስቲቫል በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን መዲና በሰቆጣ ከተማ ከነሐሴ 14 ቀን እስከ 16 2008 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሯል፡፡"የሻደይ ባህላችን ለዘላቂ ልማታችን" በሚል የተከበረው ይህ በዓል የተለያዩ ዝግጅቶችን ያካተተ ሲሆን በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች የታደሙበት ነው፡፡

Thursday, August 4, 2016


                       ኦይዳ ወረዳ
 

የኦይዳ ወረዳ በጋሞ ጎፋ ዞን ከሚገኙ አስራ አምስት ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ሸፊቴ ይባላል፡፡ ወረዳው የተመሰረተው በ1998 ዓ.ም. ነው፡፡ ኦይዳ ማለት ለም ማለት ሲሆን የብሔረሰቡና የወረዳው መጠሪያም ነው፡፡ ወረዳው በሃያ ቀበሌያት የተዋቀረ ሆኖ በደቡብ ኡባ ደብረ ፀሀይ፣ በሰሜን ገዜ ጎፋ፣ በምዕራብ ሰሜን አሪ እና በምስራቅ ደግሞ ደንባ ጎፋ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡

Wednesday, August 3, 2016


        የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሮክተሬት በ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም ተሸላሚ ሆነ፡፡

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በዘርፍ ከሚገኙ የፌዴራል የኮሙኒኬሽን አደረጃጀቶች መካከል የ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላመጡ እውቅና ተሰጥቷል፡፡

Wednesday, June 15, 2016


ባህል ለኢትዮጵያ ልማት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

 

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ዓመታዊው ባህል ለኢትዮጵያ ልማት በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡
 
 

Friday, May 20, 2016

ዓለም አቀፉ የሙዚየም ቀን ተከበረ



 የዘንድሮ የዓለም የሙዚየም ቀን‹‹ ሙዚየሞችና ባህላዊ መልክዓ ምድር!››/ Museums and Cultural Landscape/ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ጊዜ በአገራችን 14 ጊዜ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተከበረ፡፡
በተፈጥሮአዊና ባህላዊ የመልክዓ ምድር አያያዝና አጠቃቀም ፣ በጥምር ደንና የግብርና ሥርዓት  በዓለም ቅርስነት ባስመዘገበው በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መከበሩ ልዩ ያደርገዋል፡፡  በክልሉ ከተማዎች ማለትም  በሐዋሳ ፣ በአርባ ምንጭ ፣ ቱርሚ፣ በጅንካና በኮንሶ አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ከግንቦት 06   እስከ ግንቦት 12  2008 . የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውነዋል፡፡

Tuesday, May 10, 2016


በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ የዘገባ ስራዎችን የሚያግዝ ስልጠና

ለሚዲያ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው፡፡

የተለየ ትኩረት እያገኘ የመጣውን የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በተገቢው መልኩ ለማስተዋወቅ እንዲቻል የሚረዳ ስልጠና በአዳማ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ከግንቦት 2-10/2008 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ ስልጣና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡ ስልጠናው በዘርፍ ያለውን የባለሙያዎች የግንዛቤ ክፍተት ይሞላል ተብሎ የታሰበ እና በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በቱሪዝምና ሚዲያ ፎረም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ዓመታዊውን የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን ማጠናቀቂያ ፌስቲቫል

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተካሄደ፡፡

 

በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የማርች ወር የሚከበረው የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን በኢትዮጵያም ባለፉት ሰላሳ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የምታከብረው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአንድ ወር ያክል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉን ስታከብር ቆይታ ሚያዝያ 29-30/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማጠቃለያ ፊስቲቫል አዘጋጅታለች፡፡

Friday, March 4, 2016


ዓለም አቀፉ የዱር እንስሳት ቀን በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀምሯል፡፡

ፎቶ፡- የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ /ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ/

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 68ተኛ ጠቅላላ ጉባዬ የዱር እንስሳት ቀን በየዓመቱ ማርች 3/ የካቲት24/ እንዲከበር ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የዘንድሮ የዱር እንስሳት ቀጣይ ህልውና በእጃችን ነው !!  በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ 3ተኛ ጊዜ በአገራችን 2 ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

Tuesday, February 23, 2016


በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰቆጣ ከተማ ተከበረ፡፡
 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ የሆነው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በኢትዮጵያም በየዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከበር ቆይቷል፡፡ የዘንድሮው በዓል በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከአዲስ አበባ በ720 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰቆጣ ከተማ ከየካቲት 13-15/2008 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡

ለ74ኛ ጊዜ የተካሄደው የኦሮሞ ብሔር የጉጂ የገዳ ሥርዓት የስልጣን ሽግግር በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፡፡
 

በኦሮሞ ብሔር ባህል በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የገዳ ሥርዓት የስልጣን ሽግግር ለ74ኛ ጊዜ እጅግ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት በጉጂ ዞን ሜኤ ቦኮ የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

Wednesday, February 17, 2016

አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ደረሱ፡፡
አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ሲደርሱ የገዳ አካላት ከጉሚ እየወጡ ነበር፡፡ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ከኦሮሞ ባህል ማዕከል በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት የተንቀሳቀሱት ስምንት ሴቶችና አስራ አምስት ወንድ ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ 32 ልኡካንን ይዘዉ እንደመጡ የገለጹት የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ግዛዉ ተወዳዳሪዎቹ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ተመልምለው የመጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በጉጂ ኦሮሞ በበደለናና በሀርሙፋ አባገዳዎች መካከል የካቲት 13ቀን ለሚደረገዉ የስልጣን ሽግግር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡