Wednesday, October 2, 2013

ደቡብ ኦሞ እና መስህቦቿ


south omo Ethiopia
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ውስጥ ከተዋቀሩት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሰሜን ጋሞጎፋ ከፋ ዞኖች እና ደቡብ ኦሞ ዞን የኮንታ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ቤንችማጂ ዞንና ሱዳን፣ በምስራቅ ኮንሶ ልዩ ወረዳ እና በደቡብ ደግሞ ከኬንያ ትዋሰናለች፡፡ ከአ/አበባ በ755 ኪ.ሜ እና ከክልሉ መዲና አዋሣ በ525 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ደቡብ ኦሞ ዞን 23530 ስኩየር ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ሲኖራት በስምንት ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አሰተዳደር የተዋቀረ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ ነው፡፡ በከፊል የአየር ንብረቱ ቆላማ ሲሆን ከ360-3300 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ያላቸው መሬቶችም አሉ፡፡

የአርፈሳ ዋሻ

አርፈስ ዋሻ ከጂንካ በ17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው ደቡብ አሪ ወረዳ ዋና ከተማ ጋዘር በ12 ኪ.ሜ ርቀት በኋላ  ሜፀር ቀበሌ ከ2 ሰዓት መንገድ ጉዞ በኋላ በጳልጳ ንዑስ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ ዋሻው ለመድረስ ከፍተኛ ድካምና ጉልበት የሚጠይቀው አቀበት ለ2 ሠዓት ጉዞ በኋላ የሚገኘው ዋሻ ጋራው ሳይቀር በእርሻ ከታረሰው ጋራ ላይ ነው፡፡ የዋሻው 2ኛው ክፍል ለማግኘት ከዋሻው መግቢያ እስከ 2ኛው የዋሻው ክፍል ድረስ 7 ሜ ርቀት በኋላ የ3 ሜ ከፍታ መሰላል ከተወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ጠለቅ ብሎ ለመግባት አዳጋች የሆነ ጠበብ ብሎ ከ20-30 ሳ.ሜ ስፋት አለው፡፡

ቦምቢ ዋሻ

በዶርዶራና ሜፀር አጎራባች ቀበሌያት ድንበር ላይ የሚገኝ ሲሆን በስተቀኝ አቅጣጫ በዶርዶር በአፅር ንዑስ ቀበሌ በሜፀር ገናመር ንዑስ ቀበሌ ይወሰናል፡፡ ወደ ኔሪ የተፈጥሮ ድልድይ እና ሶራብ ፏፏቴ ሲሄዱ የኔሪ የተፈጥሮ ድልድይ የተወሰነ ርቀት ሲቀር በስተግራ አቅጣጫ ጥቂት ገባ ብለው ያገኙታል፡፡ በሁለት ንዑስ ቀበሌያት ድንበር ላይ በ2 ተራራ መካከል ከሚገኝ ጎርጂ ተከትሎ ከሚፈሰው የጋንፅላ ወንዝ ስር ከፏፏቴው አናት ላይ አነስተኛ ፏፏቴ ተፈጥሮበታል፡፡

የቀርከሀ ደን

ቀርከሃ በደጋና በወይና ደጋ የአየር ንበረት የሚያድግ ተክል ነው፡፡ የማደግና የመቆጥቆጥ አቅሙ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ጥቅጥቅ ያለ ደን የመመስረት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ አጠቃላይ የቀበሌው የመሬት ሽፋን 3650 ሄክታር ሲሆን ከዚህም ውስጥ 78 ሄክታሩ መሬት በቀርከሀ ደን የተሸፈነ ነው፡፡ ይህም ከቀበሌው የመሬት ሽፋን ጋር ሲነፃፀር  2.13%  ይሸፍናል፡፡ አጠቃላይ የቀርከሀ በግለሰብ ይዞታ የሚገኝ ከመሆኑ አንፃር ሕብረተሰቡ በፈለገው ጊዜና ሰዓት ለግል ግልጋሎቱ እንደሚጠቀም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ዶርዶራ ቀበሌ በደጋና በወይናደጋ የአየር ንብረት ከመገነቱ የተነሣ ለቀርከሃ ደን ምይህ ደን እያንዳንዱ አርሶ አደር በማሳው ዳር የተከለው ሲሆን በኔሪ ወንዝ ዙሪያ ክስንሰለት ጀምሮ እስከ ዱደት ደን መጠኑ እየበዛ ይዘልቃል፡፡ ደኑ በአንድ ላይ ጥቅጥቅ ብሎ 78 ሄክታር የሚሸፍን ሳይሆን ብዙም ሳይርቅ ብዙም ሳይርቅ አልፎ አልፎ የሚገኝ ነው፡፡ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ሲሆን ህብሬሰቡ ቀርከሃን ለባህላዊ ቤት መስሪያነት፣ ለቤት ሽፋን፣ አጥር ለማጠር እና የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን /ዕቃዎችን/ ለማምረት ይጠቀማሉ፡፡

ሶራብ ፏፏቴ

የሶራብ ፏፏቴ ከዶርዶራ ቀበሌ በስተምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን መስሕቡ ወዳለበት ስፍራ ሲያቀኑ መለስተኛ አቀበት እና ሜዳማ የእግር መንገድ ያለው ሲሆን አካባቢው አየር ፀቤ ደጋማ ከመሆኑ የተነሳ በተጓዙ ቁጥር መተላለፍያ መንገዱን አቋርጦ ቁልቋል እየተንደረደሩ የሚፈሱ ወራጅ ወንዞችና ጅረቶች በሚያሰሙት ድምጾች ታጅበው ወደ ፏፏቴው መድረስ ጥቂት ያህል ደቂቃዎች ሲቀርዎት ከጋርምልሲ ንኡስ ቀበሌ ክልል ውስጥ ከሚገኘው ሰንሰለታማ ተራራ ላይ ደረቱን ገልብጦ ቁልቁል የሚወርደውን ሶራብ ፏፏቴን ያስተውሉታል፡፡

አገር ተራራ  

አገር ተራራ የሚገኘው በወሰት ቀበሌ ነው፡፡ የተራራው ከፍታ ያልተለካ ቢሆንም ከ2000 ሜ በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ አንዳንድ በተራራው የወጡ ሰዎችም እንደነገሩኝ ጫፉ ሜዳ እንደሆነ ነው፡፡ የአየር ሁኔታ ደጋና በበጋ ወራት ምቹ እንደሆነ ይታወቃል፡፡         

 
የኔሪ ተፈጥሯዊ /የእግዜር/ ድልድይ
የኔሪ የተፈጥሮ ድልድይ  አሪ ወረዳ በዶርዶራ ቀበሌ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ  ጂንካ በ27 ኪ.ሜ ርቀት እና ከወረዳው ዋና ከተማ ጋዘር በስተምስራቅ አቅጣጫ በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ድልድይ የሚገኘው ከ2600 ሜትር ከባህር ወለል ከፍታ ላይ በሀገር በቀል በተለያዩ እፅዋቶችና ተክሎች ጥቅጥቅ ብሎ ከተሸፈነው ዶርዶራ ተራራ ላይ ልዩ ስሙ ጓሳ ተብሎ ከሚጠራው የተፈጥሮ ደን ውስጥ መነሻውን በማድረግ የተለያዩ የወረዳውን ቀበሌያትን እንዲሁም የጂንካ ከተማ አቋርጦ  ከሚፈሰው የኔሪ ወንዝ ላይ በደጋማ ምቹና ተስማሚ የአየር ፀባይ ካላት፣ በብዛት  የቀርከሃ ተክል፣ ስነዴ፣ ገብስ፣ አተር እና ባቄላ የመሳሰሉት ሰብሎችን በማምረት ከሚታወቀው ዶርዶራ ቀበሌ እምብርት ላይ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የኔሪ ወንዝ ማጎ ብሄራዊ ፓርክ መጠሪያ ስያሜውን ካገኘው ከማጎ ወንዝ ጋር በፓርኩ ክልል ውስጥ ከተቀላቀለ በኋላ ማሳረጊያውን በኦሞ ወንዝ ያደርጋል፡፡
 

No comments:

Post a Comment