Showing posts with label ባህል. Show all posts
Showing posts with label ባህል. Show all posts
Friday, October 6, 2017
Thursday, September 3, 2015
Monday, December 8, 2014
የካማሺ ዞን
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙት 3 ዞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማም ካማሽ ትባላለች፡፡ የክልሉ ርዕሰ
ከተማ ከሆነችው አሶሳ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በ246 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አቅጣጫ ደግሞ በ512 ኪሎ ሜትር
ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
![]() |
| ጀሎ ተራራ ካማሽ ወረዳ ጀሎ ሌቃ ቀበሌ |
የዞኑ ህዝብ ቁጥር 128,632 ሲሆን በአምስት ወረዳዎችና በ65 ቀበሌዎች የተደራጀ ነው፡፡ ዞኑን በደቡብ እና በምስራቅ
ኦሮሚያ ክልል በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ከአሶሳና ከደቡብ ሱዳን እንዲሁም በሰሜን ከመተከል ዞንና ከአማራ ክልሎች ጋር ይዋሰናል፡፡
የአየር ንብረቱ ቆላማ ሲሆን በዞኑ በብዛት ሰፍሮ የሚገኘው የጉሙዝ ብሄረሰብ ነው፡፡
Wednesday, September 17, 2014
በናና ጸማይ…..
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች
ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ደቡብ ኦሞ ዞን ስር ከተዋቀሩት 8 ወረዳዎችና አንድ የከተማ አስተዳደር መካከል የበናና ፀማይ ወረዳ አንዱነው፡፡
የወረዳው ዋና ከተማ ቀይ አፈር ከዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በ42 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳው በሰሜን
ከደቡብ አሪ እና ማሌ፣ በደቡብ ከሐመር ወረዳ፣ በስተምስራቅ ከኮንሶ በምዕራብ ከማጎ ፓርክ እና ሳላማጎ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡
በዞኑ ከሚገኙት 16 ብሔረሰቦች ውስጥ በዋናነት ሶስቱ ብሔረሰቦች የሚገኙት በዚህ ወረዳ
ውስጥ ነው፡፡ እነዚህም የበና፣ የፀማይ እና የብራይሌ ብሔረሰቦች ናቸው፡፡
Tuesday, August 26, 2014
አሸንዳ - የሰሜናዊቷ ኮከብ ከተማ ኮከብ ኩነት
በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
አማኞች ዘንድ
የጾመ ፍልሰታ
ፍጻሜን ተከትሎ
የሚከበረው የአሸንድዬ
በዓል በዋናነት
በሰሜን ኢትዮጵያ
ከሚከበሩ መንፈሳዊ
በዓላት መካከል
የሚጠቀስ ነው፡፡
የአሸንዳ ባህላዊ ጨዋታ መጠሪያ የኾነው ቄጤማ ረዥምና ለምለም እንደ ቅጠል ሰፋ ያለ ሲሆን ቁመቱ ከ80 እስከ 90 ሣ.ሜ ይኾናል፡፡
የአሸንዳ በዓል በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚከበር በሀገራችን ከሚገኙ ኩነቶች አንዱ ነው፡፡
አሸንዳ ጥንታዊና የልጃገረዶች ባህላዊ በዓል ነው፡፡ በተለይም ከአዲስ አበባ በ783 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የክልሉ መዲና
መቐለ በየዓመቱ የምታስተናግደው ይህ ፌስቲቫል ከትግራይ ወጣቶች ባለፈ ጎብኚዎችም በጉጉት የሚጠብቁት ባህላዊ ትዕይንት ሆኗል፡፡
Wednesday, October 2, 2013
መስቀልን በደንባ ጎፋ
| Gofa |
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በጋሞ ጎፋ ዞን በደምባ ጎፋ ወረዳ ተገኝተናል፡፡ ወረዳዋ
ከመዲናችን አዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ516 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ወረዳዋን በስተ ምስራቅ የዛላ ወረዳ፣
በደቡብ የገዜ ጎፋና ኦይዳ ወረዳዎች፣ በምዕራብ የመሎ ኮዛ እና በሰሜን የቁጫ ወረዳና የዳውሮ ዞን ያዋስኗታል፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋት 97,900 ሄክታር ሲሆን በ38 ቀበሌያት የተዋቀረ ነው፡፡ የወረዳው አጠቃላይ ህዝብ ብዛት
150,000 የደረሰ ሲሆን የራሱ የሆነ የቋንቋና የባህል እሴቶች ባለቤት ናት፡፡
Tuesday, December 11, 2012
ካፋና ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎቹ
በካፋ ብሔረሰብ ዘንድ የለቅሶ፣ የሰርግ፣የጸሎትና የፍቅር ዘፈኖች አሉ፡፡
በለቅሶ ወቅት ሟችን የሚያወድሱ ጀግንነቱን የሚተርኩ ዘፈኖች ይዘፈናሉ፡፡
በተመሳሳይ የሸካዎች የሰርግ ሥነ-ሥረዓትም በባህላዊ ዘፈኖቻቸው የታጀበ ነው፡፡ እነዚህ ዘፈኖች እንደ ባህሉ በሚቃኙ የባህል ሙዚቃ
መሳሪያዎች የሚደምቁ ናቸው፡፡ ጥቂቶችን እንቃኛቸው ከቲንቦ እንጀምር የትንፋሽ መሳሪያው ቲንቦ የካፋን የለቅሶ ሥረዓት በማድመቅ
ወደር የሌለው መሳሪያ ሲሆን ከእንጨት የሚሰራ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ለአዋጅ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሃይል ያለው ድምጽ በማውጣት ይታወቃል፡፡
Friday, September 14, 2012
መስቀል በአዲግራት
![]() |
| መስቀል በአዲግራት |
መስቀል በሃገራችን በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡ በተለይም የደመራ
በዓል ከፌስቲቫል ቱሪዝም ሀብታችን ውስጥ ግንባር ቀደሙን ቦታ ይይዛል፡፡ ይህንን በዓል የሰው ልጆች ሁሉ እሴት ለማድረግም ጥረቶች
ተጀምረዋል፡፡ መስቀልን በዩኔስኮ ለመመዝገብ በቅቷል፡፡
መስቀል እንደ የኢትዮጵያውያን እሴትና ባህል ከዳር ዳር የሚከበር ከአደይ
ጋር አብሮ የሚፈካ፣ ከዘመን ጋር የሚጠባ በዓል በመሆኑ ይበልጥ ደማቅ እንዲሆን አድርገዋለል፡፡
በድንቅ እሴት የተሞላውና ብዙ ሳይነገርለት የኖረው የምስራቃዊ ትግራይ ዞን
የመስቀል በዓል አንዴ ሌላ የባህል ሃብት መስህባችን ነው፡፡
Monday, March 26, 2012
ጡማኖ እና ፋቂሳ
ጡማኖ እና ፋቂሳ
ቴላሞ የጡማኖ መታሰቢያ
![]() |
| sidma tomano memoraial የጡማኖ መካነ መቃብር እና የሃገር ሽማግሌው አቶ ሲዳሞ ቢረጋ |
ከለኩ ከተማ በስምንት ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ቴላሞ ነው፤ ቴላሞ የሲዳማ አድባር ነው ሲሉ የሃገር ሽማግሌዎቹ ይገልጻሉ፡፡ አረንጓዴ ምድር ምን ማለት እንደሆነ በቴላሞ ቅጥር ግቢ ያሉት ሃገር በቀል ግዙፍ የዛፍ ዝርያዎች ለትውልድ የቆሙ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ መልከአ-ምድራዊ ውበቱ ይማርካል፤ ከደኑ መሃል በአጥር የተከበበ አንድ ቅጥር አለ፤ በዚህ ቅጥር ውስጥ የሲዳማ ነገድ አባት የሆነው የጡማኖ መቃብር ይገኛል፡፡ በስፍራው በየእጽዋቱ ስር የአረብኛ ጽሁፍ ያለባቸው ድንጋዮች ይገኛሉ፤ እንደ አካባቢው ሽማግሌዎች ገለጻ እነዚህ የአረብኛ ጽሁፍ ያለባቸው ድንጋዮች መቃብሮች ናቸው፡፡
ሲዳሞ ቢራጋ የሃገር ሽማግሌ ናቸው፤ በየግዜው ለተለያየ ጉዳይ ወደ ቴላሞ ይመጣሉ፤ ይህንን ስናጠናቅር በስፍራው ያገኘናቸውም ለተመሳሳይ ዓላማ በቴላሞ ውብ ቅጥር ግቢ ለውይይት አረፍ እንዳሉ ነው፡፡ የሲዳማ የሃገር ሽማግሌዎች የሚለብሱትን ባህላዊ አለባበስ የለበሱት አቶ ሲዳሞ ቢራጋ ስፍራውን በሚመለከት አንዳንድ ጥያቄዎችን ስናቀርብላቸው በማራኪ አተራረክ ለዛ መልሰውልናል…መነሻችን ደግሞ ቴላሞ ምንድን ነው የሚል ነበር አቶ ሲዳሞ በተረጋጋ ሁኔታ ረጃጅም የቅጥሩ ዛፎች ላይ አይናቸውን ተክለው አብራሩልን….
Subscribe to:
Posts (Atom)



