የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የባህል ማዕከል በሀገረ ሰብ የባህል ሕክምና ዙሪያ ሀገራዊ የውይይት መድረክ አዘጋጀ፡፡
የባህል መድኃኒት
ጠበብቶች እና ሳይንሳዊ ሊቃውንቶች ተቀራርቦ መስራት ላይ ችግር እንዳለባቸው ተገልጾዋል፡፡
*******
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አምስት
ኪሎ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ በሀገረሰባዊ ሕክምና ዙሪያ ሀገራዊ ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱ ሀገረሰባዊ የህክምና
ጥበባችን ከየት? ወደየት? በሚል መነሻ የቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መድሃኒት መምህራን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን
ጥናት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ተደጋግሞ የተነሳው የባህል ህክምና ጠበብት ተገቢው ቦታ እንደማይሰጣቸው፤
አስፈላጊው የሆነ ድጋፍ እንደማይደረግለትና በተደጋጋሚ ችግር ያለባቸውን የባህል ሐኪሞች ብቻ እንደመገለጫ በመቁጠር የሀገረሰባዊ
የህክምና ጥበቡን የማንቋሸሽ ተግባር እንደሚስተዋል ተነስቷል፡፡
በሌላ በኩል የሳይንስ ሊቃውንቱ ከሀገረሰባዊ እውቀት ጠበብቶች ጋር በጋራ
የመስራቱና የመቀናጀቱ ባህል አለመኖር ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የተካነችበት የህክምና ጥበብ ዛሬ ከእነህንድና ቻይና ኋላ አድርጓታል፤
የሚል መነጻጸሪያም ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ
ሽመልስ ማዕከሉ በአዋጅ በተሰጠው የስልጣን መጠን ድረስ ዘርፍ እንዲለማ እንዲህ ያሉ ውይይቶች እንዲቀጥሉ እና የሀገራችን የባህል
ሕክምና ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment