Showing posts with label ተፈጥሮ. Show all posts
Showing posts with label ተፈጥሮ. Show all posts

Friday, October 6, 2017



የየም ልዩ ወረዳ አስናቂ መስህቦች

አንገሪ ቤተ መንግስት

የየም ልዩ ወረዳ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ በ239 ኪሎ ሜትር ከክልሉ መቀመጫ ከሐዋሳ በቡታጅራ በኩል 333 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳውን በደቡብ ኦሮሚያ ክልልና ሀዲያ ዞን በሰሜን ኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞንና ሀዲያ ዞን፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 56 ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል አንዱ የሆነው የየም ብሔረሰብ በዋናነት የሚኖረው በየም ልዩ ወረዳ ክልል ውስጥ ሲሆን ከወረዳው ውጭ በጅማ ዞንና በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በብዛት ይኖራሉ፡፡   

Wednesday, October 2, 2013

ደቡብ ኦሞ እና መስህቦቿ


south omo Ethiopia
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ውስጥ ከተዋቀሩት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሰሜን ጋሞጎፋ ከፋ ዞኖች እና ደቡብ ኦሞ ዞን የኮንታ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ቤንችማጂ ዞንና ሱዳን፣ በምስራቅ ኮንሶ ልዩ ወረዳ እና በደቡብ ደግሞ ከኬንያ ትዋሰናለች፡፡ ከአ/አበባ በ755 ኪ.ሜ እና ከክልሉ መዲና አዋሣ በ525 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ደቡብ ኦሞ ዞን 23530 ስኩየር ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ሲኖራት በስምንት ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አሰተዳደር የተዋቀረ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ ነው፡፡ በከፊል የአየር ንብረቱ ቆላማ ሲሆን ከ360-3300 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ያላቸው መሬቶችም አሉ፡፡

Tuesday, December 11, 2012


ያንጉ ዲራሳ ብሔራዊ ፓርክ

የአዘሎ ስር ውበት

አዘሎ ውብና ግዙፍ ተራራ ነው፤ እንደ ሌላው ተራራ አዘሎን ከባህር ጠለል በላይ ይሔን ያክል ብሎ በሜትር በመለካት ርዝመቱን መተረክ አይቻል ይሆናል… ምክንያቱም የአዘሎ ውበቱ ከስሩ ሆኖ መታየቱ ነውና፤ ከመልካ ወረር ሜዳማ ምድር አልያም ከገዳማይቱ የተንጣለለ መስክ ሲታይ አዘሎ ርቆ የቆመ ግዙፍ ተራራ ነው፡፡ አካባቢው ዝናብ ሲያገኝ አዘሎ አረንጓዴ ካባ ይለብሳል፡፡ ዝናብ ከራቀው ግን ከል ይለብሳል፡፡ አዘሎ ክረምትና በጋ ልቡስን የሚቀይር ተራራ፤

Friday, July 20, 2012


ቱሪዝም በዳዉሮ
ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ


የዳዉሮ ዞን  ከኢትዮጵያ ዉብ ገፅታ ማሳያዎች አንዱ ነዉ፡፡ ዞኑ በደቡብ ክልል የሚገኝ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ትባላለች፡፡ ታርጫ ገስጋሽ ነገር ግን በሚሌኒየሙ ከተወለዱ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ከሐዋሳ በ282 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ ደግሞ በሻሸመኔ አድርገዉ በወላይታ ሶዶ የሚጓዙ ከሆነ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በሌላኛዉ መንገድ በጅማ አርገዉ የሚጓዙ ከሆነ ደግሞ በ479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚያገኟት ከተማ ስትሆን ከተማዋ በየግዜዉ እያስመዘገበች ባለዉ እድገት ሳቢያም የብዙዎችን ትኩረት ስባለች፡፡

      በደቡብ ከጋሞ ጎፋ በምዕራብ ከኮንታ ልዩ ወረዳ በሰሜን ምዕራብ ከኦሮምያ ክልል በሰሜን እስከ ሰሜን ምስራቅ ከከንባታ ጠንባሮ ዞን በምስራቅ ከወላይታ ዞን ይዋሰናል፡፡ ከሰሜን ምዕራብ እስከ ደቡብ ጫፍ ድረስ በጎጀብና በኦሞ ወንዞች ተፋሰስ የተከበበዉ የዳውሮ ዞን የብዙ እሴቶች ማዕከል እና እንብርት ነዉ፡፡ ከአምስት በላይ በሆኑ ብሄረሰቦች መከበቡ ዳውሮን ልዩ የባህል አምባ ያደርገዋል፡፡

Monday, January 16, 2012


ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮችና በሀይቆች የተሞላ ሲሆን፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይኅን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የዕፅዋት እና የሕዝብአሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖራት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዐይነትየአየር-ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም:-
  • ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግረ ሴ.ግ የማይበልጥ፤
  • ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል ከ1500 እስከ 2400 ሜትር፣ ሙቀታቸውም ከ16 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 30 ዲግረ ሴ.ግየሚደርስና፣ 
  • ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ30 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 50ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስ አከባቢዎች ናቸው።
ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲትእና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

Sunday, January 1, 2012

አዕዋፍ


        
          ኢትዮጵያ ሞቃታማ/ዝቅተና በሆነ መሬት የተከበበ ትልልቅ ከፍታማ የመሬት ደሴት የሆነው መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ ለልዩ ልየ የአእዋፍ ዝርያዎች መገኛ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ 862 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ ሲገኙ ከነዚህ ውስጥ16ቱ በሌላ አለም የማይገኙ ናቸው፡፡

Friday, December 23, 2011

ዕፅዋት



    ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት በደኖች መጨፍጨፍና በተፈጥሮ እፅዋት መመናመን ምክንያት በተከሰተው የመሬት መራቆት ትታወቃለች፡፡ ምንም እንኳን ስለመጀመሪያው የእፅዋት ሽፋን ገፅታ በጥቂቱ ቢታወቅም የሀገሪቱን ሀብታምነት የሚያሳዩ የተፈጥሮ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ በእንስሳት አለም እንዳለው ሁሉ ብዙ እፅዋትም በኢትጵጵያ ብቻ የሚገኙ ሲሆን ሌሎችም ብዙ መገኘት የሚገባቸው አሉ፡፡