አርባ ምንጭ ከተማ ከጥቅምት 24 እስከ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ዓመታዊውን የኢትዮጵያ ዋርደኖች ጉባኤ አስተናግዳለች፡፡
የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ወደብ ከተማ የሆነችው እና ከአዲስ አበባ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አርባ ምንጭ ያስተናገደችው
የዘንድሮው ጉባኤ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነበር፡፡
በሮሚ ሆቴል የተካሄደው ይህ ጉባኤ የ2008 ዓ.ም. እቅድ አፈጻጸም ምን ይመስል ነበር በሚል አስቀድሞ ሪፖርቱን በመገምገም
የጀመረው የፓርክ ባለሙያዎች ጉባኤ ባለድርሻ አካላትን እና መገናኛ ብዙሃንን ማሳተፉ ከወትሮው ለየት አድርጎታል፡፡ ዛሬም አልተፈቱም
በአሳለፍንው ዓመትም ቢሆን ችግሮች ነበሩ የተባሉ ሳንካዎች በጉባኤው ተነስተዋል፡፡ ከብሔራዊ ፓርኮች ለሌላው የሚተርፍ ተሞክሮ አላቸው
የተባሉ ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡ 2009 ዓ.ም. እቅድ ላይም ጉባኤው መክሯል፡፡ የኢትዮጵያ ፓርኮች ፈተና ናቸው የተባሉ ርዕሰ
ጉዳዮች በተወያዮቹ ቀርበዋል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በዞናቸው ሁለት ብሔራዊ ፓርኮች መኖራቸውን ጠቅሰው ነጭ
ሳርን ለመታደግ የዞኑ መንግስት በርካታ እርምጃዎችን ቢወስድም ርብርቡ የሁሉንም ድርሻ ያካተተ ባለመሆኑ የነጭ ሳር ህልውና አሁንም
አነጋጋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ዳውድ ሙሜ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸውን ሲያቀርቡ
ያለፈው ዓመት በርካታ የሚቆጠሩ ስራዎች የተሰራበት ቢሆንም አሁንም የተፈጥሮ ሀብታችንን ህልውና እና የፓርኮቻችንን ደህንነት የሚፈታተኑ
ችግሮች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ የግጭ መንደር አደጋ ላይ ከነበረው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማስወጣቱን ስራ እንደ ዓመቱ ታላቅ
ስኬት ይቆጠራል ብለዋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳ ጉባኤውን ያስተናገደው የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወይዘሮ አልማዝ በየሮ
ናቸው፡፡ ይህ ጉባኤ እንደ ወትሮው አውርተን የምንበተንበት ሳይሆን ቆጥረን ሃላፊነት የምንወስድበት እንዲሆን እፈልጋለሁ በሚል ነበር
ጉባኤውን በንግግር ሲከፍቱ የተናገሩት፤
አንዳንድ የጉባኤው ታዳሚዎች የጉባኤው ጊዜ ማጠር እንዳሰቡት በስፋት በመወያየት ችግሮችን ከስሩ ለማጥራት ውስንነት መፍጠሩን
ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በፊት ኦሞ፣ ስሜን እና ጋምቤላ ተካሄደው ከነበሩ ጉባኤዎች አራተኛውን ልዩ የሚያደርገው የህዝብ ክንፉ በባለቤትነት
የተሳተፈበት በመሆኑ ነው የሚለው ግን ከብዙዎች ደጋግሞ የተነሳ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment