Friday, August 26, 2016


አሸንዳ 2008 በዓል በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡
Photo; Ashenda festival in Mekelle

አሸንዳ 2008 ባህላዊ ኩነት በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው ይህ በዓል ከመቐለ ከተማ ውጪ በተንቤን አብይ አዲም በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ችለናል፡፡



ነሐሴ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት በመቐለ አክሱም ሆቴል የተደረገው ዓመታዊው የአሸንዳ ሲምፖዚየም በአሸንዳ በዓል ዙሪያ በስፋት መክሯል፡፡ የጎዳና ላይ የካርኒቫል ትእይንቱን ከየዞኑ የተውጣጡ የባህል ተጨዋቾች አድምቀውታል፡፡

ነሐሴ 16 ቀን ምሽቱን በሮማናት አደባባይ የነበረው የዋዜማ ዝግጅት እጅግ ደማቅ ሲሆን በማግስቱ ነሐሴ 16 ቀን ከሰዓት በኋላ በሮማናት አደባባይ ዋናው የአሸንዳ በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡ ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሐመድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ክብርት ወይዘሮ ታደለች ዳለቾ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና አቶ ዳዊት ኃይሉ የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ታድመውበታል፡፡

የበዓሉ ዋና አካል በሆነው የዛሬው ዝግጅት እንደ ትግራይ ልጃገረዶች ሁሉ የውጪ ዜጎችም የአሸንዳ ልብስ ለብሰው የታዩበት ነበር፡፡ የአሸንዳ በዓል ማጠናቀቂያ የነበረውና ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት በድምቀት የተከበረው የማጠቃለያ ዝግጅትም እጅግ ደማቅና የተለየ ነበር፡፡

 

  

 

No comments:

Post a Comment