ሻደይ 2008 ፌስቲቫል በድምቀት ተከበረ፡፡
Photo: shaday festival 2016 wagehimera zone
|
በአማራ ክልል ከአዲስ አበባ 720 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘዋ የዋግ ሹሞቹ መናገሻ ታሪካዊቷ የዋግኽምራ ብሔረሰብ
ዞን መዲና ይህንን ዓመታዊ ኩነት በድምቀት አስተናግደዋለች፡፡ የመሰረተ ልማት ጉብኝቶች፣ አውደ ጥናት፣ ባህላዊ ትዕይንቶችና ሌሎች
በርካታ ክዋኔዎችን ያካተተው ሻደይ 2008 ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር
አይሻ መሐመድን ጨምሮ በርካታ እንግዶች የታደሙበት ነበር፡፡
ይህ በዓል መንፈሳዊም ባህላዊም ትርጓሜ አለው፡፡ ከፍልሰታ ጾም፣ ከኖኅ ቃል ኪዳንና ከዮፍታሄ ታሪኮች ጋር ቁርኝት ያለው ሲሆን በዋናነት ልጃገረዶች ለቀናት ዝግጅት አድርገው ያከብሩታል፡፡ ሻደይ ማለት በኽምጣጋ ቋንቋ ለምለም ወይም አረንጓዴ ማለት ነው፡፡ ልጃገረዶች ቅጠሉን አገልድመው፣ በባህላዊ አልባሳት ተውበው፣ በማራኪው የዋግ ባህላዊ ጨዋታዎች እየደመቀ ነው፡፡

No comments:
Post a Comment