ዓመታዊውን የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን ማጠናቀቂያ ፌስቲቫል
በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተካሄደ፡፡
በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የማርች ወር የሚከበረው የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን በኢትዮጵያም ባለፉት ሰላሳ ቀናት በተለያዩ
ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የምታከብረው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአንድ ወር ያክል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉን ስታከብር
ቆይታ ሚያዝያ 29-30/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማጠቃለያ ፊስቲቫል አዘጋጅታለች፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተዘጋጀው የማጠቃለያ ፌስቲቫል በዲንሾ የፓርኩ ዋና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢና በሮቤ ከተማ የተከበረ
ሲሆን በፓናል ውይይትና በመስክ ጉብኝት የታገዘ ነበር፡፡ በዱር እንስሳት ሀብቶቻችንና በባሌ ተራሮች የብዝሃ ህይወት አቅም ላይ
እንደመነሻ በቀረቡ የጥናት ጽሑፎች ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በስሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች የተደረገው የቤተሰባዊ
ጉብኝት ጉዞ የዚህ በዓል አካል እንደነበረ ይታወሳል፡፡
No comments:
Post a Comment