ባህል ለኢትዮጵያ ልማት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡
የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ዓመታዊው ባህል ለኢትዮጵያ
ልማት በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡
ከሰኔ 8-9/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ካምፓስ የሚካሄደው የዘንድሮው
ጉባኤ ሲከፈት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተወካይና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር
የሆኑት አቶ ደስታ ካሣ ጉባኤ የሀገራችን ባህል ለልማት የሚውልበትን አቅጣጫ የሚያሳዩ የጥናትና ምርምር ጽሑፎች የሚቀርቡበት መሆኑን
ገልጸው ይህንን መሰል የትብብር ጉባኤዎችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት
እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎው ሰባት የመነሻ ጥናት ጽሑፎች ቀርበው ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ነገም
ቀጥሎ ይውላል፡፡
No comments:
Post a Comment