Friday, March 3, 2017

121ኛው የአድዋ ድል በዓል በብሄራዊ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ በአድዋ ከተማ ተከብሯል፡፡








121ኛው የአድዋ ድል በዓል በብሄራዊ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ በአድዋ ከተማ ተከብሯል፡፡ የአድዋ 121ኛ የድል በዓል በአድዋ ከተማ ጦርነቱ በተከናወነበት የሶሎዳ ተራራ ግርጌ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ ‹‹ የአድዋ ድል ብዝኃነን ላከበረቻት  ኢትዮጵያ ድህነትን ለማሸነፍ የሚያስችል ህያው አብነት ነው››!! በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

Monday, December 12, 2016



የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚደግፉ ልምዶችን ለመቅሰም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በኬኒያ እየተደረገ ነው፡፡



Monday, November 7, 2016



4ኛው የኢትዮጵያ ዋርደኖች ጉባኤ፤ 

አርባ ምንጭ ከተማ ከጥቅምት 24 እስከ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ዓመታዊውን የኢትዮጵያ ዋርደኖች ጉባኤ አስተናግዳለች፡፡ የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ወደብ ከተማ የሆነችው እና ከአዲስ አበባ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አርባ ምንጭ ያስተናገደችው የዘንድሮው ጉባኤ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነበር፡፡

Thursday, October 20, 2016



አዲሱ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ብራንድ እና ቀጣዩ የመገናኛ ብዙኃን ሚና

=====================================
ኢትዮጵያ የመለዮ ስያሜውን LAND OF ORIGINS ያደረገ አዲስ የቱሪዝም አርማ እና መለዮ ስያሜ ይፋ አድርጋለች፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጉት አዲሱ የመለዮ ስያሜ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያክል የአስራ ሦስት ወር ጸጋ በሚል ሲያገለግል የኖረውን ብራንድ ስያሜ የሚተካ ነው፡፡

Friday, October 14, 2016


የመስቀል በዓል አከባበር በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ
ጢያ ትክል ድንጋይ-ሶዶ ወረዳ
 

የመስቀል በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበት፣ የተነፋፈቁ ናፍቆታቸውን የሚወጡበት፣ ያለፈው ጊዜ ምን እንደሚመስል መጪው ጊዜ ምን መሆን እንዳለበት የሚወስኑበት ለክብረ በዓሉ በሰላም ላደረሳቸው ፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡበት ለወደፊቱም መልካም ምኞታቸውን የሚገልፁበት አጋጣሚ ነው፡፡ መስቀል የክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ማህበረሰባዊ ልማዱን ከትውልድ ትውልድ ከሚያስተላልፍባቸው ሀገራዊ ልማዶች መካከል አንዱ በዓል ነው፡፡

Saturday, September 10, 2016


ጎፋ ጋዜ ማስቃላ 2009 በዛላ ወረዳ ይከበራል፡፡
 

በጎፋ ብሔረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል ጎፋ ጋዜ ማስቃላ 2009 በዛላ ወረዳ በድምቀት ይከበራል፡፡ ከመስከረም 9-10 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚከበረው ይህ በዓል በጎፋ ብሔረሰብ የተለዩ እሴቶች የሚደምቅና ጊያ ካንሶ በሚባለው የመስቀል በዓል ሽኝት ሥነ-ሥርዓት የሚታጀብ ነው፡፡

Friday, August 26, 2016


አሸንዳ 2008 በዓል በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡
Photo; Ashenda festival in Mekelle

አሸንዳ 2008 ባህላዊ ኩነት በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና በመቐለ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው ይህ በዓል ከመቐለ ከተማ ውጪ በተንቤን አብይ አዲም በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ችለናል፡፡