Friday, August 26, 2016


ሻደይ 2008 ፌስቲቫል በድምቀት ተከበረ፡፡
Photo: shaday festival 2016 wagehimera zone
ሻደይ 2008 የባህል ፌስቲቫል በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን መዲና በሰቆጣ ከተማ ከነሐሴ 14 ቀን እስከ 16 2008 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሯል፡፡"የሻደይ ባህላችን ለዘላቂ ልማታችን" በሚል የተከበረው ይህ በዓል የተለያዩ ዝግጅቶችን ያካተተ ሲሆን በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች የታደሙበት ነው፡፡

Thursday, August 4, 2016


                       ኦይዳ ወረዳ
 

የኦይዳ ወረዳ በጋሞ ጎፋ ዞን ከሚገኙ አስራ አምስት ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ሸፊቴ ይባላል፡፡ ወረዳው የተመሰረተው በ1998 ዓ.ም. ነው፡፡ ኦይዳ ማለት ለም ማለት ሲሆን የብሔረሰቡና የወረዳው መጠሪያም ነው፡፡ ወረዳው በሃያ ቀበሌያት የተዋቀረ ሆኖ በደቡብ ኡባ ደብረ ፀሀይ፣ በሰሜን ገዜ ጎፋ፣ በምዕራብ ሰሜን አሪ እና በምስራቅ ደግሞ ደንባ ጎፋ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡

Wednesday, August 3, 2016


        የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሮክተሬት በ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም ተሸላሚ ሆነ፡፡

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በዘርፍ ከሚገኙ የፌዴራል የኮሙኒኬሽን አደረጃጀቶች መካከል የ2008 ዓ.ም. አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላመጡ እውቅና ተሰጥቷል፡፡

Wednesday, June 15, 2016


ባህል ለኢትዮጵያ ልማት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

 

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ዓመታዊው ባህል ለኢትዮጵያ ልማት በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡
 
 

Friday, May 20, 2016

ዓለም አቀፉ የሙዚየም ቀን ተከበረ



 የዘንድሮ የዓለም የሙዚየም ቀን‹‹ ሙዚየሞችና ባህላዊ መልክዓ ምድር!››/ Museums and Cultural Landscape/ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ በአገራችን ለ14 ጊዜ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተከበረ፡፡
በተፈጥሮአዊና ባህላዊ የመልክዓ ምድር አያያዝና አጠቃቀም ፣ በጥምር ደንና የግብርና ሥርዓት  በዓለም ቅርስነት ባስመዘገበው በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መከበሩ ልዩ ያደርገዋል፡፡  በክልሉ ከተማዎች ማለትም  በሐዋሳ ፣ በአርባ ምንጭ ፣ በቱርሚ፣ በጅንካና በኮንሶ አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ከግንቦት 06   እስከ ግንቦት 12  2008 ዓ.ም የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውነዋል፡፡

Tuesday, May 10, 2016


በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ የዘገባ ስራዎችን የሚያግዝ ስልጠና

ለሚዲያ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው፡፡

የተለየ ትኩረት እያገኘ የመጣውን የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በተገቢው መልኩ ለማስተዋወቅ እንዲቻል የሚረዳ ስልጠና በአዳማ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ከግንቦት 2-10/2008 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ ስልጣና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡ ስልጠናው በዘርፍ ያለውን የባለሙያዎች የግንዛቤ ክፍተት ይሞላል ተብሎ የታሰበ እና በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በቱሪዝምና ሚዲያ ፎረም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ዓመታዊውን የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን ማጠናቀቂያ ፌስቲቫል

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተካሄደ፡፡

 

በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የማርች ወር የሚከበረው የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን በኢትዮጵያም ባለፉት ሰላሳ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የምታከብረው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአንድ ወር ያክል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉን ስታከብር ቆይታ ሚያዝያ 29-30/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማጠቃለያ ፊስቲቫል አዘጋጅታለች፡፡