Thursday, December 5, 2013
Monday, December 2, 2013
የብዝኃናነት ስብጥርና የቀለሙ ፋይዳ
Harer |
ወጥ ከሆነ ቀለም ህብራዊነት ውበት አለው፡፡ አበቦች ከእጽዋት በበለጠ ሳቢና የመንፈስ እርካታ ምክንያት
የሆኑበት ሚስጥር ህብረ ቀለማዊነታቸው ነው፡፡ እንደማንኛውም የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች ሁሉ ክቡሩን የሰው ልጅም ህብራዊ ስብጥሩ ያደምቀዋል፡፡
ለሰው ልጅ ህብራዊነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ የሰው ልጅ ህብራዊነት ከአያሌ ነገሮች ይቀዳል፡፡ ቋንቋው፣ ኃይማኖቱ፣
ባህሉ፣ መልከዓ ምድራዊ መኖሪያው እና የአካባቢው ተጽእኖ እና ሌሎች እልፍ መነሾዎች አሉት፡፡
የግዮን ላይ ለዛ
Blue Nile |
ግዮን ያለ ሀሳብ ይወርዳል፡፡ የዘፍጥረት መጽሐፍ ኢትዮጵያን ይከባል ቢለውም በአራት ወገን ከተከፈሉት አራት ወንዞች
አንዱና ኤደን ገነትን የሚያጠጣ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ አባይ አባይ ብለን የተቃኘንለት ግዙፍ ወንዝ የ1440 ኪሎ ሜትር ጉዞውን
ከሚጀምርበት በራፍ….ግዮንን ተማምኖ ኑሮውን የሚኖር ሰው ነው፡፡ ህብርሰው ምህረት ይባላል፡፡ አስራ ሁለት ዓመታት እንዳለፉት የሚናገረው
ህብር ሰው ሰዎችን ከጢስ አባይ ከተማ ዳርቻ ወደ ጢስ አባይ ፏፏቴ ያሻግራል፡፡
Wednesday, October 2, 2013
ደቡብ ኦሞ እና መስህቦቿ
south omo Ethiopia |
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ውስጥ
ከተዋቀሩት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሰሜን ጋሞጎፋ ከፋ ዞኖች እና ደቡብ ኦሞ ዞን የኮንታ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች፣
በምዕራብ ቤንችማጂ ዞንና ሱዳን፣ በምስራቅ ኮንሶ ልዩ ወረዳ እና በደቡብ ደግሞ ከኬንያ ትዋሰናለች፡፡ ከአ/አበባ በ755 ኪ.ሜ
እና ከክልሉ መዲና አዋሣ በ525 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ደቡብ ኦሞ ዞን 23530 ስኩየር ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ሲኖራት በስምንት
ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አሰተዳደር የተዋቀረ ዞን ነው፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ጂንካ ነው፡፡ በከፊል የአየር ንብረቱ ቆላማ ሲሆን
ከ360-3300 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ያላቸው መሬቶችም አሉ፡፡
መስቀልን በደንባ ጎፋ
Gofa |
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በጋሞ ጎፋ ዞን በደምባ ጎፋ ወረዳ ተገኝተናል፡፡ ወረዳዋ
ከመዲናችን አዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ516 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ወረዳዋን በስተ ምስራቅ የዛላ ወረዳ፣
በደቡብ የገዜ ጎፋና ኦይዳ ወረዳዎች፣ በምዕራብ የመሎ ኮዛ እና በሰሜን የቁጫ ወረዳና የዳውሮ ዞን ያዋስኗታል፡፡ የወረዳው የቆዳ ስፋት 97,900 ሄክታር ሲሆን በ38 ቀበሌያት የተዋቀረ ነው፡፡ የወረዳው አጠቃላይ ህዝብ ብዛት
150,000 የደረሰ ሲሆን የራሱ የሆነ የቋንቋና የባህል እሴቶች ባለቤት ናት፡፡
ወረታ እንደ ቱሪስት መዳረሻ
werta city |
ለምለሙ የፎገራ ምድር የምርታማነት ቀጠና ነው፡፡ ትርፍ አምራች በሆነው ምድር የተከበበችው ወረታ ከተማ በአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ከባህር ዳር ጎንደር በሚወስደው ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡
ወረታ ከአዲስ አበባ ኪሎ ሜትር ከክልሉ ርእሰ ከተማ ከባህር ዳር በ55 ኪሎ ሜትር፣ ከጎንደር ከተማ 120 ኪሎ
ሜትር፣ ከደብረ ታቦር ከተማ ደግሞ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ 14,097 ወንድ እና 14,379 ሴት በድምሩ
28,475 ህዝብ የሚኖርባት ወረታ በ1942 ዓ.ም ገደማ ነበር የተቆረቆረችው፡፡ ይሁን እንጂ ፈጣን ልማቷን ተከትሎ በሚሊኒየሙ
ማለትም በ2000 ዓ.ም በከተማ አስተዳደርነት ተደራጀች፡፡
የሀላባ ልዩ ወረዳ የቱሪስት መዳረሻዎች
የሀላባ ልዩ ወረዳ
በክልላችን ካሉ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ከሚገኙባቸው ልዩ ወረዳዎች
አንዱ ነው፡፡ በሀላባ ልዩ ወረዳ የተለያዩ ሰው ሰራሽ፣ ታሪካዊ እና የተፈጥሮ ቅርሶች ተከማችተው ይገኙበታል፡፡ እነዚህ የቱሪስት
መዳረሻዎች መካከል የአርቶ ፍል ውሃ፣ የስፋሜ ዋሻ፣ የኑርአህመድ መካነ-መቃብር፣ የብላቴ ፏፏቴ/ፋማ/ ፓርክ፣ የአሶሬ ደን እና
ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች የውጭ ምንዛሬ ከማምጣታቸውም በላይ ለተለያዩ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የቻሉ
በመሆናቸው አሁንም በእነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ቦታው ክፍት መሆኑን በመጠቆም ነው፡፡
Monday, May 27, 2013
ኮንሶ…….
የኮንሶ
ህዝብ ገናና ነው፡፡ ስራ ስሙን ከፍ አድርጎት ከጥንት እስከ ዛሬ ብዙ ይወራለታል፡፡ የወረዳ ስያሜ በብሔረሰቡ መጠሪያ ስም ኮንሶ
ይባላል፡፡ በደቡብ ክልል ሲገኝ በባህል ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ መዳረሻ እየሆነ በመጣው የደቡብ ኦሞ በራፍ የሚገኝ አካባቢ ነው፡፡
ኮንሶ- ካራት |
አዲሲቷ ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ሥር ከሚገኙ አምስት ወረዳዎች አንዱ የሆነው ኮንሶ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ595 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከሀዋሳ ደግሞ በ365 ኪ.ሜትር
ርቀት ላይ በደቡባዊ ምስራቅ ቀጠና ይገኛል፡፡ ለደቡብ ኦሞ ጅንካ ከተማና
ለያቤሎ ሞያሌ መስመር ቀጠና መሆኑ የንግድ ማእከል እንዲሆንም አድርጎታል፡፡
የሲዳማ ዞን የቱሪስት መዳረሻዎች
BONORA FALL-SIDAMA |
ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ
ሎካ አባያ ብሔራዊ ፓርክ በሲዳማ ዞን የሚገኝ ለዞኑ
ብቸኛ ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡ ፓርኩ በሎካ አባያ ወረዳ ከሐዋሳ ከተማ 73 ኪሎ ሜትር እና ከሎካ አባያ ወረዳ ዋና ከተማ ከሀንጣጤ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል
፡፡ ፓርኩ በታላቁ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ /Great east African rifty vally/ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሞቃት
አየር ንብረት ማለትም ወደ በረሃማ የተጠጋ የስነ - ምህዳር ባህሪ ይታይበታል፡፡ የታላቁ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ስነ-ምህዳር
Great east African rifty vally system አካል የሆነው የአባያ ሐይቅ የዚህ ፓርክ አካል ነው፡፡ የአባያ ሀይቅን
ጨምሮ ብላቴ ወንዝ ፣ጊዳዎ ወንዝ እና ኮላ ወንዝ በዚህ ስፍራ መኖራቸው ለፓርኩ የተለያዩ ብዝሃ ህይወት
/bio-diversity/ እንዲኖሩት አድርጎታል ፡፡
አፍሪካና ቱሪዝም
የዛሬ 50 ዓመት ከመነጣጠል አንድነትን የመረጡት አፍሪካውያን ግማሽ ምእተ አመት
የሚሆን የጋራ ጉዞ አድርገዋል፡፡ ዘንድሮ ይህንን ልደት መዲናችን አዲስ አበባ እያከበረችው ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ዝግጅት
ምክንያት አድርገን አፍሪካና ቱሪዝምን ለመቃኘት ወደድን፡፡
African un |
አህጉራችን አፍሪካ በቀላሉ የሚጋዙ ሀብቶቿን በቀኝ ግዛት ዘመን ቢበዘበዝባትም፡፡
ተፈጥሮ የለገሰቻት ተወስዶ የማያልቀው ጸጋዋ ግን ዛሬም የትናንት ቀኝ ገዢ ሀገራትን በስጎመዠ መልኩ እንደነበር አለ፡፡ አፍሪካ
አሁን የዓለም ጎብኚዎች መዳረሻ እየሆነች ነው፡፡ ሀምሳ አራት ገደማ ሀገራት የተጠለሉባት ይህች አህጉር እንደ ኪሊማንጃሮ ካሉ
ተራሮች እስከ ዝቅተኛው የምድር አካል ዳሉል ድረስ የተካተተባት ምድር ናት፡፡ ታላቁ የሰሀራ በርሐ መገኛ አፍሪካ ነው፡፡ በሰው
ልጅ ታሪክ የተለየ ቦታ ካላቸው የተፈጥሮ ሀብቶች አንዱ የሆነውና ረጅሙ ወንዝ ናይል የአፍሪካውያን ነው፡፡
Sunday, April 14, 2013
Monday, March 18, 2013
Sunday, March 17, 2013
Saturday, March 16, 2013
ምርጥ 10 የስልጤ ዞን የቱሪስት መዳረሻዎች
የስልጤ ዞን በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ
መንግስት ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው፡፡ የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት
ሲሆኑ በዞኑ የሚኖረው ህዝብ ብዛት ደግሞ ይደርሳል፡፡ የዞኑ ርእሰ ከተማ ወራቤ ከአዲስ አበባ በ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
የምትገኝ እና በፍጥነት እያደገች ያለች ከተማ ናት፡፡ ስልጤ ዞኑ በበርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች ከክልሉ አርአያ ከሚባሉ ዞኖች
አንዱ ነው፡፡ ከእነዚህ መልካም እና ስኬታማ ተግባራት መካከል ደግሞ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች ተጠቃሽ
ናቸው፡፡ በየዓመቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት ፕሮሞሽናል ቁሳቁሶችን ያዘጋጃል፣ ያትማል፣ ያሰራጫል፤ የተለያዩ የባህል እሴቶቹ
እንዲጠኑ፣ ቋንቋውን የተመለከቱ ምርምሮች እንዲደረጉ በፈጠረው ምቹ እድል በክልሉ የዘርፉ የልቀት ቀጠና ከሚባሉ ዞኖች መካከል ሊጠቀስ
ችሏል፡፡
በዚህ ረገድ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የዞኑን ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና
ሰው ሰራሽ መስህቦችን በመለየት ደረጃ በማውጣት እና በማስተዋወቅ እያከናወነ ያለው ተግባር እንደሀገርም የተለየ ያደርገዋል፡፡ እኛም
በዞኑ ምርጥ 10 ተብለው የተለዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን በወፍ በረር እንቃኛቸዋለን፡፡
ሀረ ሸይጣን ሀይቅ
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አጎዴ በተባለው ቀበሌ የሚገኘው ይህ
ሀይቅ ከአዲስ አበባ ወራቤ አርባምንጭ በተዘረጋው አስፋልት ላይ ቡታጅራ ከተማን አልፈው 9 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኃላ በስተምስራቅ
1.2 ኪሎ ሜትር ገባ ብለው የሚያገኙት ሐይቅ ነው፡፡ ሀራ ሸይጣን ሀይቅ የሚገኝበት ወረዳ ዋና ከተማ ቅበት ሲሆን ሀይቁ ከቅበት
3.4 ኪሎ ሜትር እንዱሁም ከወራቤ 30.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ይህን ሀይቅ የተለየ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ተፈጥሮአዊ
አቀማመጡ፣ የሀይቁ ገጽታ እና ስለሀይቁ የሚነገሩ ታሪኮች ዋናውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ የገበቴ ቅርጽ ያለው ሀረ ሸይጣን ሀይቅ ከላይኛው
የመሬት ገጽታ በታች ተንጣሎ የተኛ በየወቅቱ የውሃውን ቀለም የሚቀያይር ጎብኚዎች አፋፉ ላይ ሆነው ድንጋይ በመወርወር ሊያስገቡ
የማይችሉበት መሆኑ ጎብኚ የበለጠ እንዲማረክና ትእንግርት እንዲሆንበት አድረጓል፡፡ በሀይቁ 1 ኪሎ ሜትር አቅራቢያ ሌላ አስገራሚ
አይናጌ የተባለ ድንቅ ዋሻም ይመለከታሉ፡፡ በዞኑ የተዘጋጀው ሀረ ሸይጣን ሀይቅን የተመለከተ መረጃ ሀይቁን ሲገልጸው በሀይቁ ዙሪያ
የሚደረግ ጉብኝትና ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም በማይለቅ ብዕር የሚጻፍ የህሊና ታሪክ እንደሆነ ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ሲል አስፍሯል፡፡
የሜኤኒት ጎልዲያ መስህቦች
በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎች አንዱ የሆነው የሜኤኒት ጎልዲያ
ወረዳ ርእሰ ከተማ ባቹማ ትባላለች፡፡ ባቹማ ከአዲስ አበባ በ591 ኪሎ ሜትር ከሚዛን ደግሞ በ87 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ
ወረዳው የሜኤኒት ብሔረሰብ መገኛም ነው፡፡
የባንዲሊ የተፈጥሮ ዋሻ
በቤንች ማጂ ዞን የቱሪስቶችን ቀልብ
የሚስቡ በርካታ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መስህቦች ይገኛሉ፡፡ በዞኑ በየጊዜው አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን ማግኘት የተለመደ ክስተት
ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በመኤኒት ጎልዲያ ወረዳ መኖሩ የማይታወቅ በይዘቱና በመስህብነቱ ወደር የማይገኝለት የተፈጥሮ ዋሻ በአካባቢ
ነዋሪዎች ጥቆማ ተገኝቷል፡፡ ዋሻውን የአካባቢ ነዋሪዎች ቀፎ ለመስቀልና የጫካ ማር ከዱር ለመቁረጥ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እንዳገኙት
ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም የተፈጥሮ መስህቡን በማጥናት በዞኑ የተፈጥሮ መስህቦች ዝርዝር ውስጥ ሊካተት ችሏል፡፡
የቱሪዝም ፀጋ በቤንች ማጂ
ቱሪዝም በአሁኑ ሰዓት በቤንች ማጂ
ዞንም በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርፍ ደህንነት ቀናሽ በመሆኑ ለዜጎች በተለይም ለሴቶችና ለወጣቶች የስራ ዕድል
ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ምዕራብ ዞኖች ፈርጥ በሆነችው ቤንች ማጂ ዞን
በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ ህዝብ ማእከል ከመሆኗ ጋር
ተዳምሮ የዞኑ ብሔረሰብና ህዝቦች መልካም እሴት ታክሎት ዞኑን የቱሪስት መዳረሻ ከማድረጉም በላይ ለሀገርና ለውጭ ሀገር ቱሪስቶች
የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በጥራትና በብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል፡፡ በመሆኑም በዞኑ
ቀልብን የሚስቡና የሚማርኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦች ሲገኙ የተወሰኑትን ለመቃኘት እንሞክራለን፡፡
ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ
የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ በቤንች ማጂ
ዞን በማጂ ወረዳ በሙይ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን የክልሉ ትልቁ ፓርክ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ በ870 ኪሎ ሜትር ከሚዛን ከተማ 242
ኪሎ ሜትር ከማጂ ከተማ ደግሞ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የኦሞ ፓርክ ልዩ ልዩ የዱር እንሰሳትና ዕፅዋቶች ሲገኙበት
የተለያዩ 75 አጥቢዎች 325 አእዋፍ ዓይነቶች ይገኙበታል፡፡ በፓርኩ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ውድንቢዎች፣ የመጋላ ቆርኪ መንጋ፣ ሳላዎች፣
የሜዳ ፍየሎች ወዘተ ይገኛሉ፡፡ ውድንቢ በኢትዮጵያ በኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኝ የዱር እንሰሳ ነው፡፡ ያሉበት አካባቢ በባለሙያ
የተጠረቡ በሚመስሉ የድንጋይ ንጣፍ የተነጠፈና በለመለሙ ቄጤማዎች ያሸበረቀ ነው፡፡ በስፍራው የተለያየ የሙቀት መጠንና ጣዕም ያላቸው
ፍል ውኃዎች መኖራቸው ለተመራማሪዎች የምርምርና ለባለሀብቱ ደግሞ
የኢንቨስትመንት መስክ ይከፍታል በሚል ኦሞ ፓርክን የመጪው ጊዜ የልማት ቀጠና አስብሎታል፡፡
Friday, March 15, 2013
6ኛው የኢትዮጵያ ፓትረያሪክ
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማይ ፓትረያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ |
የክርስትና እና የእስልምና ኃይማኖቶች ሂደትና ውጤት ከኢትዮጵያ ማንነት
ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዛሬ ትደርስ ዘንድ ከፍተኛውን አስተዋጾ በመወጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተ ክርስቲያን ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ዓለም ኢትዮጵያን ከቤተ ክርስቲያኗ እሴቶች ጋር በአንድ ሊመለከት የቻለበትም ሚስጥር ሀገሪቱና
ቤተ ክርስቲያኗ በዘመናት ሂደት ከፈጠሩት አብሮነት የተፈጠረው ኢትዮጵያ ገናና ታሪክ በመነሳት ነው፡፡
5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያሪክ የነበሩት
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማይ፤ ፓትረያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ
ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያኗን በዓለም አደባባይ የቀደመ ክብሯ ስፍራውን እንዲይዝ አድርገው የ20ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸውን ባከበሩ
ማግስት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፤ ይህንን ተከትሎ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንትና የአለም ኃይማኖቶች የክብር
ፕሬዝዳንት የነበሩት የኢትዮጵያ ፓትረያሪክ ሞት የዓለም ትኩረት ሳበ፤ ይህ ትኩረት እስከ 6ኛው ፓትረያሪክ ምርጫና የምርጫ ሂደት
ድረስ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንደሳበ ቀጥሎ ነበር፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)