Friday, August 8, 2014


የፎቶና ቪዲዮ ባለሙያዊ አዚዝ አህመድ ድንቅ ሥራዎች ተመረቁ፡፡
 

ፕሮፌሽናል የጉዞ ፎቶ ግራፈሩና የቪዲዮ ባለሙያ የሆነው አዚዝ አህመድ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ያነሳቸው የአእዋፍ ፎቶ ምስሎችና የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብቶች የሚያሳየውን የአጭር ድምጽና ምስል የቱሪዝም ዘጋቢ ፊልሙን ትናንት ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ላይ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል አስመርቋል፡፡

ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ በኢትዮጵያዊ በዚህ መልኩ ሲሰራ የመጀመሪያ ሊባል የሚችለው ድንቅ ስራ ክቡር አቶ አሚን አብዱልቃድር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ክቡር አቶ እውነቱ ብላታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ በተገኙበት ተመርቋል፡፡

የጉዞ ፎቶግራፈሩ ጥንካሬ እውን ያደረጋቸው እነኚህ የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ መስህቦች የሚያስተዋውቁ ስራዎች በሀገራችን ቱሪዝም ልማት ጎብኚዎችን በመሳብ የሚኖራቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡ ዶክመንተሪውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአየር መንገደኞች በመቅረብ ላይ ያለ መሆኑን ስራውን ከደገፉት አንዱ የሆኑት የፍራንክፈርት ዙኦሎጂካል ሶሳይቲ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ገልጸዋል፡፡

አዚዝ አህመድ በተለየ መልኩ ትኩረታቸውን በአእዋፍና ተፈጥሮ መስህቦች ዙሪያ አድርጎ በመስራት ስኬታማ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች አንዱ ነው፡፡  

Wednesday, July 23, 2014


የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል በሐዋሳ እየተከበረ ነው፡፡

የራሳቸው የቀን አቆጣጠር ካላቸው የሀገራችን ብሔሮች አንዱ የሆነውና በየዓመቱ በልዩ ድምቀት የዘመን መለወጫ በዓሉን የሚያከብረው የሲዳማ ብሔረሰብ የፍቼ በዓል በታላቅ ድምቀት በሐዋሳ እየተከበረ ነው፡፡


ዝግጅቱ በዋናነት ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን ከሰዓት በኋላ በሲዳማ ባህል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት መከበሩን የቀጠለ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ እና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የብሔረሰቡ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ታድመውበታል፡፡
ዝግጅቱን በተመለከተ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ወርቅነህ ፍላቴ ሲናገሩ፤ ፍቼ በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የምታስመዘግበው ዓለም አቀፍ ቅርስ ይሆናል ብለዋል፡፡
 
በዓሉ በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን የበዓሉ ዋና መዲና ሐዋሳ በዓሉን በከፍተኛ ዝግጅት እያስተናገደችው ነው፡፡


 
 

 

Thursday, December 5, 2013

የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ

Monday, December 2, 2013





የብዝኃናነት ስብጥርና የቀለሙ ፋይዳ

Harer
ወጥ ከሆነ ቀለም ህብራዊነት ውበት አለው፡፡ አበቦች ከእጽዋት በበለጠ ሳቢና የመንፈስ እርካታ ምክንያት የሆኑበት ሚስጥር ህብረ ቀለማዊነታቸው ነው፡፡ እንደማንኛውም የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች ሁሉ ክቡሩን የሰው ልጅም ህብራዊ ስብጥሩ ያደምቀዋል፡፡ ለሰው ልጅ ህብራዊነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ የሰው ልጅ ህብራዊነት ከአያሌ ነገሮች ይቀዳል፡፡ ቋንቋው፣ ኃይማኖቱ፣ ባህሉ፣ መልከዓ ምድራዊ መኖሪያው እና የአካባቢው ተጽእኖ እና ሌሎች እልፍ መነሾዎች አሉት፡፡

                                                        የግዮን ላይ ለዛ

Blue Nile
ግዮን ያለ ሀሳብ ይወርዳል፡፡ የዘፍጥረት መጽሐፍ ኢትዮጵያን ይከባል ቢለውም በአራት ወገን ከተከፈሉት አራት ወንዞች አንዱና ኤደን ገነትን የሚያጠጣ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ አባይ አባይ ብለን የተቃኘንለት ግዙፍ ወንዝ የ1440 ኪሎ ሜትር ጉዞውን ከሚጀምርበት በራፍ….ግዮንን ተማምኖ ኑሮውን የሚኖር ሰው ነው፡፡ ህብርሰው ምህረት ይባላል፡፡ አስራ ሁለት ዓመታት እንዳለፉት የሚናገረው ህብር ሰው ሰዎችን ከጢስ አባይ ከተማ ዳርቻ ወደ ጢስ አባይ ፏፏቴ ያሻግራል፡፡