የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል በሐዋሳ እየተከበረ ነው፡፡
የራሳቸው
የቀን አቆጣጠር ካላቸው የሀገራችን ብሔሮች አንዱ የሆነውና በየዓመቱ በልዩ ድምቀት የዘመን መለወጫ በዓሉን የሚያከብረው የሲዳማ
ብሔረሰብ የፍቼ በዓል በታላቅ ድምቀት በሐዋሳ እየተከበረ ነው፡፡
ዝግጅቱ በዋናነት ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን ከሰዓት በኋላ በሲዳማ ባህል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት መከበሩን የቀጠለ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ እና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የብሔረሰቡ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ታድመውበታል፡፡
ዝግጅቱን
በተመለከተ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ወርቅነህ ፍላቴ ሲናገሩ፤ ፍቼ በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ
በዩኔስኮ የምታስመዘግበው ዓለም አቀፍ ቅርስ ይሆናል ብለዋል፡፡
በዓሉ
በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን የበዓሉ ዋና መዲና ሐዋሳ በዓሉን በከፍተኛ ዝግጅት እያስተናገደችው ነው፡፡
No comments:
Post a Comment