Wednesday, March 20, 2013
Monday, March 18, 2013
Sunday, March 17, 2013
Saturday, March 16, 2013
ምርጥ 10 የስልጤ ዞን የቱሪስት መዳረሻዎች
የስልጤ ዞን በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ
መንግስት ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው፡፡ የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት
ሲሆኑ በዞኑ የሚኖረው ህዝብ ብዛት ደግሞ ይደርሳል፡፡ የዞኑ ርእሰ ከተማ ወራቤ ከአዲስ አበባ በ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
የምትገኝ እና በፍጥነት እያደገች ያለች ከተማ ናት፡፡ ስልጤ ዞኑ በበርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች ከክልሉ አርአያ ከሚባሉ ዞኖች
አንዱ ነው፡፡ ከእነዚህ መልካም እና ስኬታማ ተግባራት መካከል ደግሞ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች ተጠቃሽ
ናቸው፡፡ በየዓመቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት ፕሮሞሽናል ቁሳቁሶችን ያዘጋጃል፣ ያትማል፣ ያሰራጫል፤ የተለያዩ የባህል እሴቶቹ
እንዲጠኑ፣ ቋንቋውን የተመለከቱ ምርምሮች እንዲደረጉ በፈጠረው ምቹ እድል በክልሉ የዘርፉ የልቀት ቀጠና ከሚባሉ ዞኖች መካከል ሊጠቀስ
ችሏል፡፡
በዚህ ረገድ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የዞኑን ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና
ሰው ሰራሽ መስህቦችን በመለየት ደረጃ በማውጣት እና በማስተዋወቅ እያከናወነ ያለው ተግባር እንደሀገርም የተለየ ያደርገዋል፡፡ እኛም
በዞኑ ምርጥ 10 ተብለው የተለዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን በወፍ በረር እንቃኛቸዋለን፡፡
ሀረ ሸይጣን ሀይቅ
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አጎዴ በተባለው ቀበሌ የሚገኘው ይህ
ሀይቅ ከአዲስ አበባ ወራቤ አርባምንጭ በተዘረጋው አስፋልት ላይ ቡታጅራ ከተማን አልፈው 9 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኃላ በስተምስራቅ
1.2 ኪሎ ሜትር ገባ ብለው የሚያገኙት ሐይቅ ነው፡፡ ሀራ ሸይጣን ሀይቅ የሚገኝበት ወረዳ ዋና ከተማ ቅበት ሲሆን ሀይቁ ከቅበት
3.4 ኪሎ ሜትር እንዱሁም ከወራቤ 30.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ይህን ሀይቅ የተለየ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ተፈጥሮአዊ
አቀማመጡ፣ የሀይቁ ገጽታ እና ስለሀይቁ የሚነገሩ ታሪኮች ዋናውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ የገበቴ ቅርጽ ያለው ሀረ ሸይጣን ሀይቅ ከላይኛው
የመሬት ገጽታ በታች ተንጣሎ የተኛ በየወቅቱ የውሃውን ቀለም የሚቀያይር ጎብኚዎች አፋፉ ላይ ሆነው ድንጋይ በመወርወር ሊያስገቡ
የማይችሉበት መሆኑ ጎብኚ የበለጠ እንዲማረክና ትእንግርት እንዲሆንበት አድረጓል፡፡ በሀይቁ 1 ኪሎ ሜትር አቅራቢያ ሌላ አስገራሚ
አይናጌ የተባለ ድንቅ ዋሻም ይመለከታሉ፡፡ በዞኑ የተዘጋጀው ሀረ ሸይጣን ሀይቅን የተመለከተ መረጃ ሀይቁን ሲገልጸው በሀይቁ ዙሪያ
የሚደረግ ጉብኝትና ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም በማይለቅ ብዕር የሚጻፍ የህሊና ታሪክ እንደሆነ ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ሲል አስፍሯል፡፡
የሜኤኒት ጎልዲያ መስህቦች
በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎች አንዱ የሆነው የሜኤኒት ጎልዲያ
ወረዳ ርእሰ ከተማ ባቹማ ትባላለች፡፡ ባቹማ ከአዲስ አበባ በ591 ኪሎ ሜትር ከሚዛን ደግሞ በ87 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ
ወረዳው የሜኤኒት ብሔረሰብ መገኛም ነው፡፡
የባንዲሊ የተፈጥሮ ዋሻ
በቤንች ማጂ ዞን የቱሪስቶችን ቀልብ
የሚስቡ በርካታ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መስህቦች ይገኛሉ፡፡ በዞኑ በየጊዜው አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን ማግኘት የተለመደ ክስተት
ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በመኤኒት ጎልዲያ ወረዳ መኖሩ የማይታወቅ በይዘቱና በመስህብነቱ ወደር የማይገኝለት የተፈጥሮ ዋሻ በአካባቢ
ነዋሪዎች ጥቆማ ተገኝቷል፡፡ ዋሻውን የአካባቢ ነዋሪዎች ቀፎ ለመስቀልና የጫካ ማር ከዱር ለመቁረጥ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እንዳገኙት
ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም የተፈጥሮ መስህቡን በማጥናት በዞኑ የተፈጥሮ መስህቦች ዝርዝር ውስጥ ሊካተት ችሏል፡፡
የቱሪዝም ፀጋ በቤንች ማጂ
ቱሪዝም በአሁኑ ሰዓት በቤንች ማጂ
ዞንም በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርፍ ደህንነት ቀናሽ በመሆኑ ለዜጎች በተለይም ለሴቶችና ለወጣቶች የስራ ዕድል
ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም የደቡብ ምዕራብ ዞኖች ፈርጥ በሆነችው ቤንች ማጂ ዞን
በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ ህዝብ ማእከል ከመሆኗ ጋር
ተዳምሮ የዞኑ ብሔረሰብና ህዝቦች መልካም እሴት ታክሎት ዞኑን የቱሪስት መዳረሻ ከማድረጉም በላይ ለሀገርና ለውጭ ሀገር ቱሪስቶች
የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በጥራትና በብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል፡፡ በመሆኑም በዞኑ
ቀልብን የሚስቡና የሚማርኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦች ሲገኙ የተወሰኑትን ለመቃኘት እንሞክራለን፡፡
ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ
የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ በቤንች ማጂ
ዞን በማጂ ወረዳ በሙይ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን የክልሉ ትልቁ ፓርክ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ በ870 ኪሎ ሜትር ከሚዛን ከተማ 242
ኪሎ ሜትር ከማጂ ከተማ ደግሞ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የኦሞ ፓርክ ልዩ ልዩ የዱር እንሰሳትና ዕፅዋቶች ሲገኙበት
የተለያዩ 75 አጥቢዎች 325 አእዋፍ ዓይነቶች ይገኙበታል፡፡ በፓርኩ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ውድንቢዎች፣ የመጋላ ቆርኪ መንጋ፣ ሳላዎች፣
የሜዳ ፍየሎች ወዘተ ይገኛሉ፡፡ ውድንቢ በኢትዮጵያ በኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኝ የዱር እንሰሳ ነው፡፡ ያሉበት አካባቢ በባለሙያ
የተጠረቡ በሚመስሉ የድንጋይ ንጣፍ የተነጠፈና በለመለሙ ቄጤማዎች ያሸበረቀ ነው፡፡ በስፍራው የተለያየ የሙቀት መጠንና ጣዕም ያላቸው
ፍል ውኃዎች መኖራቸው ለተመራማሪዎች የምርምርና ለባለሀብቱ ደግሞ
የኢንቨስትመንት መስክ ይከፍታል በሚል ኦሞ ፓርክን የመጪው ጊዜ የልማት ቀጠና አስብሎታል፡፡
Friday, March 15, 2013
6ኛው የኢትዮጵያ ፓትረያሪክ
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማይ ፓትረያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ |
የክርስትና እና የእስልምና ኃይማኖቶች ሂደትና ውጤት ከኢትዮጵያ ማንነት
ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዛሬ ትደርስ ዘንድ ከፍተኛውን አስተዋጾ በመወጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተ ክርስቲያን ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ዓለም ኢትዮጵያን ከቤተ ክርስቲያኗ እሴቶች ጋር በአንድ ሊመለከት የቻለበትም ሚስጥር ሀገሪቱና
ቤተ ክርስቲያኗ በዘመናት ሂደት ከፈጠሩት አብሮነት የተፈጠረው ኢትዮጵያ ገናና ታሪክ በመነሳት ነው፡፡
5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያሪክ የነበሩት
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማይ፤ ፓትረያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ
ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያኗን በዓለም አደባባይ የቀደመ ክብሯ ስፍራውን እንዲይዝ አድርገው የ20ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸውን ባከበሩ
ማግስት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፤ ይህንን ተከትሎ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንትና የአለም ኃይማኖቶች የክብር
ፕሬዝዳንት የነበሩት የኢትዮጵያ ፓትረያሪክ ሞት የዓለም ትኩረት ሳበ፤ ይህ ትኩረት እስከ 6ኛው ፓትረያሪክ ምርጫና የምርጫ ሂደት
ድረስ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንደሳበ ቀጥሎ ነበር፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)