Thursday, June 7, 2012


                                       ራስ ግንብ
ይህ ቤተመንግስት የተገነባው በከፍታ ቦታ ላይ ሲሆን ከፋሲል ቤተ-መንግስት በስተሰሜን በኩል 300 ሜትር ርቀት ላይ ነው፡፡  ይህ ቤተመንግስት ባለሁለት ፎቅ ሆኖ ከመሰረቱ ሰፊና ወፍራም ግንባታ ያለው ሲሆን ወደላይ እየቀጠነ የሚሄድ ነው፡፡

ሁለት ወታደሮች (ማማዎች) ሲኖሩት ሶስተኛው ግን በባለ አራት ማዕዘን ማማው መሐል ይገኛል፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የአሰራር ስልቶች በዘመኑ ሰቀላ ግንብ ወይም ከበሮ ግንብ በመባል ታወቃሉ፡፡ በተለይ አራተኛውና ትልቁ ማማ (Tower) ይህ ቤተመንግስት ግርማ ሞገሱ የበለጠ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ ይህ ሁሉ ውበትና የአሰራር ጥበብ የፈሰሰበት ቢሆንም  ከአፄ  ፋሲል  ቤተመንግስት (ግንብ) በመጠኑ ያነሰነው፡፡ ነገር ግን በቅርጹና በአሰራር ጥበቡ ተመሳሳይነት አለው፡፡

                  ራስ ግንብ  ሙዚየም
               RAS GENB MUSUME


የራስ ግንብ ባለአራት ማዕዘን ሆኖ በከፍታ ቦታ ላይ የተገነባ በመሆኑ የጎንደርን ውበት በበለጠ መልኩ አጉልቶ ያሳያል፡፡

በዚህ ቤተ-መንግስት ላይ የሚታዩት ማማዎች (ታወሮች) ለጥበቃና ከርቀት መመልከቻ ሆነው የሚያገለግሉ ቢሆንም ነገር ግን ባለአራት ማዕዘን ሰቀላ ግንብ ግን ለተለያየ አገልግሎት ይውሉ እንደነበር ይገለፃል፡፡

በሁለተኛው ፎቅ ላይ ለመፀዳጃ ቤት የሚያገለግሉ ክፍሎች ሲገኙ አራት ሰፋፊ ክፍሎች በውጭ በኩል የሚያሳዩ በረንዳዎች (Balcones) በግንቡ ሁሉም ገጽታ በኩል ያሉት የቤተ-መንግስቱን ውበት የጠበቁለት ሆነው በተለይ ወደታችኛው ምድር ቤት ስንወርድ ከአምስት እስከ ስድስት ክፍሎች የተለያዬ ስፋት ያላቸው ለተለያዬ አገልግሎት የሚውሉ ሲኖሩት በተለይ በጣም ሰፊ የሆነው ክፍል ሳሎን በመሆን ያገለግላል፡፡

ወደሁለተኛው ፎቅ ሁለት የመወጣጫ ደረጃዎች ያሉትና በፈለጉት ቢጠቀሙ ወደተመሳሳይ ክፍል የሚወስድና የሚያደርስ ነው፡፡ አንደኛው ከደቡብ ወደ ምዕራብ ካለው መግቢያ በር የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪም ከቤተ-መንግስቱ አጠገብ ከሚገኘው የመንበረ ጽባህ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ጋር ያገናኛል፡፡ የቤተ-መንግስቱ አሰራር ስልትና የመወጣጫ ደረጃው 1682-1706 .. ከተገነባው የአድያም ሰገድ እያሱ ቤተ-መንግስት ኮርቻ ግንብ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡

ራስ ግንብ በአሁኑ ጊዜ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን አገልግሎት የሚሰጡ በቁጥር ወደ 159 የሚሆኑ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶች ለምሳሌ ያህል ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ቁምሳጥን፣ አልጋዎች፣ የቅብ ስዕል ስራዎች የሞሉት ሲሆን ሁሉም በደህና ሁኔታ እየተጠበቁ ኖረው አሁን ለረጅም ዘመናት በላያቸው ላይ ተዘግቶባቸው የነበረው ይህ ቤተ-መንግስት ለእይታ በቅቷል፡፡ ከእነዚህ እድሜ ጠገብ የቤት ውስጥ ቁሳቁስና የቤተ-መንግስቱ አካል በጣሊያን ወረራ ጊዜ አገልግሎት ይሰጡ ስለነበር የተጠገኑና የታደሱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የጥንታዊ ጎንደር ዘመንን እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ሌላ አካባቢ ከሚገኙ ቤተ-መንግስቶች የተወሰዱ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

በአፈ-ታሪክ እንደምንሰማው የራስ ግንብ የተገነባው በአፄ ፋሲል ዘመን ለወንድማቸው ልጅ ለራስ ቢትወደድ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያና መታሰቢያ እንዲሆን ነው የተሰራው ሲባል ሌሎች ደግሞ የራስ ግንብ የተሰራው በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን እንደሆነ ይገልፃሉ፤ ፡፡ ለዚህም ዋቢ የሚያደርጉት አንድ የየመን ሀገር ጎብኝ ሀሰን አል አሚን የሚባል ጎንደርን 1648 .. በጎበኘበት ጊዜ በተጨማሪም ቻርልስ ፓንሴት የተባለ ፈረንሳዊ ጎንደርን በጎበኙበት ወቅት ሁለቱም በጽሁፋቸው ውስጥ ስለ ራስ ግንብ አልጠቀሱም፡፡ ይህ ሆኖ ራስ ወልደ ጊዮርጊስ በዚህ ግንብ አልተጠቀሙም፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው በዚህ ጊዜ በመተማ አካባቢ በወራሪ ጠላት ወይም በሽምቅ ተዋጊዎች ተገድለው ስለሞቱ በዚህ መቆየታቸው ያጠራጥራል የሚሉም አሉ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ራስ ግንብ በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን ራስ ስሁል ሚካኤል ይኖሩበት እንደነበር በታሪክ ተዘግቦ ይገኛል፡፡ ምናልባት በዚህ ጊዜ በነበራቸው ጠንካራ የግሪክ ነጋዴዎችና የግብጽ ጥበበኞች (Clerics) ግንኙነት ይህን ቤተ-መንግስት ውበቱን ጨምረውለትና አሻሽለውት እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ራስ ስሁል ሚካኤል በዘመኑ የጦር መሪ (ሚኒስትር) ብቻ ሳይሆኑ ፍፁም ኃይለኛ ገዥ መሆናቸው ይነገራል፡፡ በዚህ ወቅት ቀስ በቀስ ዘመነ መሳፍንት የተጀመረበት ስለሆነ ይህ ዘመንም በታሪክ ዘንድ ዘመነ መሳፍንት በመባል ይታወቃል፡፡ ዘመኑም 1769 . እንደነበር ይታወቃል፡፡ የነገስታቶቹ ጉልበትና ኃይል እየደከመ በመምጣቱ ስልጣኑ በአጠቃላይ በራስ ስሁል ሚካኤል እጅ ወደቀ፡፡ ይህንም 1769 . በዕድሜ ልጁ የሆነውን የቋረኛው እያሱ ልጅ (የእቴጌ ምንትዋብ የልጅ ልጅ) እዩአስን በመግደል አፀደቁት፡፡ በዚህ ጊዜ የነገስታቱ ዘውድ ወደቀና ራስ ስሁል ሚካኤል ሁሉንም ተቆጣጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜም የንጉስ ተክለጊዮርጊስ ፍፃሜ ሆነ፡፡ በተለይ 1780 በስፋት እንደሚታወቀው የጎንደር የመጨረሻው ዘመን ወይም ፍፃሜ በይነ ነገስታት ዘጎንደር በመሆኑ ከዚህ በኋላ በሀገራችን ለረጅም ዘመን ቋሚ መናገሻ ከተማ አልታየም፡፡


No comments:

Post a Comment