የመጀመሪያው የባህል ኢንዱስትሪ የንግድ ፌስቲቫል ከነገ ማክሰኞ የካቲት 27-2004 ዓ.ም
ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ከአርባ በላይ የክልል ተሳታፊዎች ለዝግጅቱ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ዝግጅቱ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሮክተሬት የተዘጋጀ ነው፡፡
ዜና-ሀገሬ ሚዲያ
በዓይነቱ የተለየ የባህል ኢንዱስትሪ ልማትን ያቀፈ የመጀመሪያው የባህል ኢንዱስትሪ የንግድ ፌስቲቫል ከነገ ማክሰኞ የካቲት 27 ቀን ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ዝግጅቱን ለመካፈል የክልል ተሳታፊዎች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ከአዲስ አበባ እና ከክልሎች በድምሩ ከመቶ በላይ ተሳታፊዎች ሲሳተፉ፤ ከአምስት ኪሎ እስከ አራት ኪሎ ባለው ቦታ የሚዘረጋው ይህ ለአራት ቀናት የሚቆየው ዝግጅት የባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች የሚቀርቡበት ንግድ ትርኢት፣ የባህል አልባሳት ሾው እና ሲምፖዚየም ያካተተ ሲሆን ያዘጋጀው በኢፊዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሮክተሬት ነው፡፡
ነገ የሚከፈተው ይህ ዝግጅት በነገው ዕለት በብሄራዊ ሙዚየም አዳራሽ በጉዳዩ ላይ የሚመክር ሲምፖዚየም እንደሚያስተናግድም አቶ አካሉ ወልደማርያም በኢፊዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሮክተሬት አስተባባሪ ገልጸውልናል፡፡
No comments:
Post a Comment