ዜና
የስልጤ ዞን 6ኛው የቋንቋ፣የታሪክና የባህል ሲምፖዚየም በወራቤ ከተማ በድምቀት ተካሄደ፡፡
ዜና፡- ሀሚኮ
ሐራ ሸይጣን ሐይቅ-ስልጤ Haro Shetan lake |
መጋቢት 23 ቀን 2004 ዓ.ም በወራቤ ለስድስተኛ ግዜ የተካሄደው ሲምፖዚየም የተለያዩ
ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡበትም ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ወ/ሮ ራውዳ ሲራጅ በስልጥኛ ቋንቋ እደገት ዙሪያ ጥናት ያቀረቡ
ሲሆን ቋንቋው እንዳያድግ ሳንካ ተብለው ለጥናቱ በተዘዋወሩበት ወቅት ከብሄረሰቡ ሽማግሌዎች የተሰነዘሩትን አስተያየት ተቀብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በስልጤ ዞን የማይዳሰሱ ቅርሶች ዙሪያ በወ/ሪት ነኢማ አብዱራሃማን መሪነት
የቀረበው ጥናትም በወፍ በረር ዞኑ ያሉትን የቅርስ ሃብቶች ያሳየ ነበር፡፡ በስልጤ ብሄረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ሥረዓት ዙሪያ አቶ
ሸርፈዲን ሰርሞሎና አቶ ነስሮ አለሙ ያቀረቡት የጥናት ጽሁፍ ትኩረት ስቦ ነበር፡፡
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል የአረብኛ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑትና በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የነበሩ እስላማዊ ሱልጣኔት
ላይ ሰፊ የታሪክ ጥናት በማጥናት የሚታወቁት አቶ መሃመድ ሰይድ መርተውታል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ
የሆኑት አቶ ሳኒ ረዲ
"በስልጤ ባህል፣ቋንቋና ታሪክ ላይ ለሚያጠኑ እና ለሚደክሙ ባለሙያዎች ተቋማትና
ግለሰቦች እውቅና ሊሰጥ፣ሊሸለሙ ይገባል ….በቀጣይም ለዚህና ይህን መሰል ለሆኑ ተግባራት ቦርድ መቋቋም አለበት "ብለዋል፡፡
፡፡