Tuesday, May 10, 2016


በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ የዘገባ ስራዎችን የሚያግዝ ስልጠና

ለሚዲያ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው፡፡

የተለየ ትኩረት እያገኘ የመጣውን የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በተገቢው መልኩ ለማስተዋወቅ እንዲቻል የሚረዳ ስልጠና በአዳማ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ከግንቦት 2-10/2008 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ ስልጣና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡ ስልጠናው በዘርፍ ያለውን የባለሙያዎች የግንዛቤ ክፍተት ይሞላል ተብሎ የታሰበ እና በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በቱሪዝምና ሚዲያ ፎረም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ዓመታዊውን የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን ማጠናቀቂያ ፌስቲቫል

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተካሄደ፡፡

 

በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የማርች ወር የሚከበረው የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን በኢትዮጵያም ባለፉት ሰላሳ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የምታከብረው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአንድ ወር ያክል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉን ስታከብር ቆይታ ሚያዝያ 29-30/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማጠቃለያ ፊስቲቫል አዘጋጅታለች፡፡

Friday, March 4, 2016


ዓለም አቀፉ የዱር እንስሳት ቀን በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀምሯል፡፡

ፎቶ፡- የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ /ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ/

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 68ተኛ ጠቅላላ ጉባዬ የዱር እንስሳት ቀን በየዓመቱ ማርች 3/ የካቲት24/ እንዲከበር ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የዘንድሮ የዱር እንስሳት ቀጣይ ህልውና በእጃችን ነው !!  በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ3ተኛ ጊዜ በአገራችን ለ2ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

Tuesday, February 23, 2016


በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰቆጣ ከተማ ተከበረ፡፡
 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ የሆነው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በኢትዮጵያም በየዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከበር ቆይቷል፡፡ የዘንድሮው በዓል በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከአዲስ አበባ በ720 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰቆጣ ከተማ ከየካቲት 13-15/2008 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡

ለ74ኛ ጊዜ የተካሄደው የኦሮሞ ብሔር የጉጂ የገዳ ሥርዓት የስልጣን ሽግግር በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፡፡
 

በኦሮሞ ብሔር ባህል በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የገዳ ሥርዓት የስልጣን ሽግግር ለ74ኛ ጊዜ እጅግ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት በጉጂ ዞን ሜኤ ቦኮ የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

Wednesday, February 17, 2016

አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ደረሱ፡፡
አባ ገዳ ቱር የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ዛሬ እኩለ ቀን መኤ ቦኮ ሲደርሱ የገዳ አካላት ከጉሚ እየወጡ ነበር፡፡ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ከኦሮሞ ባህል ማዕከል በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት የተንቀሳቀሱት ስምንት ሴቶችና አስራ አምስት ወንድ ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ 32 ልኡካንን ይዘዉ እንደመጡ የገለጹት የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ግዛዉ ተወዳዳሪዎቹ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ተመልምለው የመጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በጉጂ ኦሮሞ በበደለናና በሀርሙፋ አባገዳዎች መካከል የካቲት 13ቀን ለሚደረገዉ የስልጣን ሽግግር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡