የቦንጋ ብሔራዊ ቡና ሙዚየም ተመረቀ፡፡
በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነውና በደቡብ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ሚያዝያ 6 ቀን
2007 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተመረቀው ብቸኛው የቡና ሙዚየም በሚሌኒየሙ መሰረተ ድንጋዩ
የተጣለ ሲሆን ዓላማውም ካፋ የቡና መገኛ መሆኗን ለማረጋገጥ፤ በሀገሪቱ ከቡና ጋር ተያይዞ የሚገኙ እሴቶችንና የቡናን ብዝሃ ህይወት
የተመለከቱ ስብስቦችን ለማኖርና ለትውልድ ለማሻገር ሲሆን ከቡና ጋር ተያይዞ ምርምርና ጥናት ለሚያደርጉም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሙዚየም
ነው፡፡ ደረጃውን የጠበቀው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ከዚህ በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment