አንድ ምሳ በማንኩሽ
Mankush |
ማንኩሽ በጣም ጥንታዊ ቀጠና ናት፤
እንደ አክሱም ሮሐ ጎንደርና ሸዋ አንድ ወቅት የሃገሪቱ የፖለቲካ ቀጠና ሆና አገልግላለች፡፡ ይህ ታሪኳ ከታላቁ የዳኣማት ስርወ
መንግስት የሚጀምር ነው፡፡ የ2005 ዓ.ም የዓለም ቱሪዝም ቀንን ያስተናገደው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የበዓሉን ተጓዦች ካስተናገደበት
ስፍራ አንዱ ማንኩሽ ነበረች፡፡ ማንኩሽ ከመድረሳችን በፊት አሻግሮ ይመለከተን የነበረው ጉባ ተራራ ነበር፡፡ ማንኩሽ ስንደርስም
ከተማዋን ቁልቁል እየተመለከተ ጠበቀን… የማንኩሽ ህዝብ በሆታ ሲቀበለን ጉባ ግን እንደተኮፈሰብን ተያየን፡፡ ከከተማዋ 35 ኪ.ሜትር
ርቀት ላይ የሚገኘው ጉባ ተራራ ለጉባ ወረዳ መጠሪያም ሆኗል፡፡