የጎንደር ከተማ አስተዳደር
ህዝቡን በማሳተፍ ያሰራው እና
ጥር 9/2004 ዓ.ም የተመረቀው የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት
ሐውልቱን
ቀራጺ ብዙነህ ተስፋ የቀረጸው ሲሆን በፋይበር ግላስ የተሰራ ነው፡፡ ከአራት መቶ ሺ ብር የበለጠ ገንዘብ ፈጅቷል፡፡ በመሃል ጎንደር
ፒያሳ ላይ የቆመው ይህ ሐውልት ከአጼ ቴዎድሮስ ባለ ሶስት ሜትር ሐውልት በተጨማሪ የልጃቸው የልኡል አለማየሁ እና የሴባስቶፖል
መድፍ ምስሎች በልጥፍ ተቀርጸውበታል፡፡ ጎንደር ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ያሬድ ግርማ ባቋቋመው ድርጅት /ራእይ ለትውልድ/ አማካኝነት
የታቀደውን የአቴ ቴዎድሮስ መታሰቢያ የትውልድ ማእከል ለማቋቋም በዞብል አካባቢ የመሰረተ ድንጋዩ ተጥሏል፡፡ ይህ ማእከል ቤተ-መጻህፍት፣ሙዝየምና
የላቁ ተማሪዎች የሚማሩበት አዳሪ ት/ቤትን ያካትታል፡፡ የህንጻው ዲዛይን በአልቲሜት ፕላን/አርክቴክት በእግዚአብሄር አለበል/ ያለክፍያ
የተሰራ ሲሆን ኪነ-ህንጻው ከጎንደር ቀደምት የኪነ--ህንጻ ጥበብ ጋር የተቀራረበ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment