Friday, October 2, 2015



አዲግራት የመስቀል በዓልን በድምቀት እያከበረች ነው፡፡




ሳውላ ጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል እያስተናገደች ነው፡፡


የደምባ ጎፋ ወረዳና የሳውላ ከተማ አስተዳደር በጋራ የሚያዘጋጁትና የጎፋ ብሔረሰብን የመስቀል በዓል አከባበር ምክንያት አድርጎ የተዘጋጀው የጎፋ ጋዜ ማስቃላ የባህል ፌስቲቫል በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ 

Tuesday, September 8, 2015

ለመላው ኢትዮጵያውያን፣
በየትኛው የዓለም ጥግ ላላችሁ ወገኖቻችን፣
ለቱሪዝምና ባህል ልማቱ ዘረፍ ባለሙያዎችና ቤተሰቦችና
ለቱባ መጽሔት ደንበኞቻችን በሙሉ
ሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን ሃ/የተ/የግ/ማህበር መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ! ይጠብቃትም፤

Thursday, September 3, 2015

Monday, August 31, 2015

መስቀልን በደምባ ጎፋ
ጎፋ ጋዜ ማስቃላ፤
ከመስከረም 9-10/2008 ዓ.ም.

በሳውላ ከተማ

አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፣ ባዛርና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው፡፡




የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሬክቶሬት፣የፋሽንና ዲዛይነሮች ማህበራትና ሜኖናይት ኢኮኖሚክ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን / MEDA/ በመተባበር የኢትዮጵያ ፋሽን አዲስ  ገልፅታ /New Images of Ethiopian Sustainable Fashion/ በሚል መሪ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የባህል ልብስ አምራቾች ፤ ዲዛይነሮች ሌሎች መሰል አካላት ባሳተፈ መልኩ አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፤ ባዛርና አውደ ርዕይ ከነሐሴ 26 እስከ ነሐሴ 30 2007 ዓ.ም በኦሮሞ የባህል ማዕከል ይከናወናል፡፡


Wednesday, August 19, 2015

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስትጨርስ፤
ዓመታዊ የጎብኚዎቿን ቁጥር 2.16 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዳለች፡፡
በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ገቢ እያስገኘ መጥቷል፡፡ የፈረንጆቹ 2012 ዓመት 1 ቢሊዮን ያክል ጎብኚ የቱሪስት ፍሰት ተመዝግቦ 1.03 ትሪሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ በዚሁ ዓመት አፍሪካ ድርሻ 34 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ሀገራችን የመጀመሪያውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስታጠናቅቅ በ750 ሺ የውጪ ጎብኚዎች ተጎብኝታ ያገኘችው ገቢ 2 ቢሊየን ብር ደርሶ ነበር፡፡