Tuesday, September 8, 2015
Thursday, September 3, 2015
Monday, August 31, 2015
አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፣ ባዛርና አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው፡፡
የባህል
ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሬክቶሬት፣የፋሽንና ዲዛይነሮች ማህበራትና ሜኖናይት ኢኮኖሚክ ዴቨሎፕመንት
አሶሴሽን / MEDA/ በመተባበር የኢትዮጵያ ፋሽን አዲስ ገልፅታ /New Images of Ethiopian Sustainable
Fashion/ በሚል መሪ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የባህል ልብስ አምራቾች ፤ ዲዛይነሮች ሌሎች መሰል አካላት ባሳተፈ
መልኩ አገር አቀፍ የፋሽን ትርዒት፤ ባዛርና አውደ ርዕይ ከነሐሴ 26 እስከ ነሐሴ 30
2007 ዓ.ም በኦሮሞ የባህል ማዕከል ይከናወናል፡፡
Wednesday, August 19, 2015
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስትጨርስ፤
ዓመታዊ የጎብኚዎቿን ቁጥር 2.16 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዳለች፡፡
በከፍተኛ ፍጥነት
እያደገ የመጣው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ገቢ እያስገኘ መጥቷል፡፡ የፈረንጆቹ 2012 ዓመት 1 ቢሊዮን ያክል ጎብኚ የቱሪስት
ፍሰት ተመዝግቦ 1.03 ትሪሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ በዚሁ ዓመት አፍሪካ ድርሻ 34 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ሀገራችን
የመጀመሪያውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስታጠናቅቅ በ750 ሺ የውጪ ጎብኚዎች ተጎብኝታ ያገኘችው ገቢ 2 ቢሊየን ብር ደርሶ
ነበር፡፡
Tuesday, August 18, 2015
የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ጋር በመሆን ከሚያዚያ 1ቀን 2007ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርት ላይ በኮኮብ ደረጃ የመመደብ ስራ የጀመረ ሲሆን በቅድሚያም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች ላይ የደረጃ ምደባ ስራው ተከናውኗል፡፡ በዚህም መሰረት በኮኮብ ደረጃ የመመደቡ ስራ ተጠናቆ ውጤቱ ነሐሴ 2,2007 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ ሆኗል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ጋር በመሆን ከሚያዚያ 1ቀን 2007ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሚገኙ ሆቴሎችና ሪዞርት ላይ በኮኮብ ደረጃ የመመደብ ስራ የጀመረ ሲሆን በቅድሚያም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች ላይ የደረጃ ምደባ ስራው ተከናውኗል፡፡ በዚህም መሰረት በኮኮብ ደረጃ የመመደቡ ስራ ተጠናቆ ውጤቱ ነሐሴ 2,2007 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ ሆኗል፡፡
Wednesday, July 8, 2015
ኢትዮጵያ የ2015 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ፤
የአውሮፓ የቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት ኢትዮጵያን የባህላዊ ቱሪዝም መዳረሻ ብሎ መርጧታል፡፡ ይህው ካውንስል በ2015
የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ በሚልም ነው የመረጣት፡፡ ይህን ሽልማት በማስመልከት የኢፊዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር
አቶ አሚን አብዱልቃድር ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ሰይድና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ታደሰ
ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሽልማቱን በይፋ ሐምሌ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በብሔራዊ ቤተ መንግስት በሚደረግ ስነ ስርዓት
እንደምንቀበል ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ለዙምባቤ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ዓመታዊ የዓለም የተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻነት ሽልማት በማግኘት ኢትዮጵያ
ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን በዘንድሮው ሽልማት ከ31 በላይ ሀገራት ዕጩ ነበሩ፡፡ ይህንን ሽልማት በብሔራዊ ቤተ መንግስት
በሚደረገው ስነ ስርዓት ስንቀበል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በአመራርነት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ልማት ላበረከቱት የላቀ
የአመራርነት ሚና እውቅና የሚቸራቸው ይሆናል፡፡
ሽልማቱን ለመስጠት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው የአውሮፓ የቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት
ቀናት ቆይታው በኢትዮጵያ የሚገኙ መዳረሻዎችንና ባህላዊ እሴቶችን የሚጎበኝ ይሆናል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)



